ያ ሁሉ ወጣት እንደ ቅጠል ረግፎ፣ ካለፈው ከደረሰው እንደ መማር ዛሬም ጠበንጃ መወልወል አሳዛኝ ነገር ነው። ክፉ ልክፍት! ደም የማይጠግብ አእምሮ!! የወጣቶች በአጭር መቀጨት፣ የእናቶች በሀዘን መሰበር፣ የአዛውንቶች ያለ ጧሪ ቀባሪ መቅረት፣ የሃገር መቆርቆዝ የማያስደነግጠው ልብ ከጠላት በላይ ጨካኝ ነው። ሰው ሌሎች ላይ ከደረሰው፣ ከጎረቤቱ ይማራል። እሱ ቢቀር እንዴት በራስ ላይ ከደረሰው መማር ያቅታል?!
ለማንኛውም ወጣት ሆይ! ለራስህ እወቅበት። በስምህ የሚምለው ሁሉ ተቆርቁሮልህ እንዳይመስልህ። ጀግና ጀግና የሚልህ ጀግና ስለሆንክ አይደለም። እየሸነገለህ ነው። ራሱንም ቤተሰቡንም ከእሳቱ አርቆ ነው አንተን የሚማግደው። ካንተ ሞት በኋላ ልጅህን፣ እናትህን ዞሮ አያይም። ግፋ ቢል ነገ ካንተ ሞት በኋላ የሰማእታት ሀውልት ብሎ የድንጋይ ክምር ቢያቆምልህ ነው። ይሄ ላንተም ለቤተሰብህም የሚጠቅመው ነገር የለም። ህዝብ ማደንዘዣ፣ ሌላ እልቂት ማቀጣጠያ እንጂ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor
Forwarded fromIbnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

August 5, 2026 331