الْأَدَبُ الثَّالِثُ: سَمِّ اللهَ فِي ابْتِدَاءِ أَكْلِكَ وَشُرْبِكَ قَائِلًا (بِسْمِ اللهِ)، وَكُلْ بِيَمِنِكَ، وَكُلْ مِمَّا يَلِيكَ، فَإِذَا فَرَغْتَ فَالْعَقْ أَصَابِعَكَ، وَقُلِ (الحَمْدُ للهِ).
ሶስተኛው፦ መመገብ ወይም መጠጣት ስትጀምር “ቢስሚላህ” በማለት የአላህን ስም አውሳ፤ በቀኝ እጅክ ተመገብ/ጠጣ፤ ፊት ለፊትክ ካለው ብላ፤ ስትጨርስ ጣቶችህን ላስ፤ “አልሐምዱ ሊላህ” በል።
ማብራሪያ
፦ ይህ አደብ
የአመጋገብ አደብ
በመባል የሚጠራ ሲሆን በውስጡ
ስድስት(6)
ነጥቦችን ይዟል;
1•
መመገብ/መጠጣት ከመጀመራችን በፊት የአላህን ስም ማውሳት እንዳለብን
;
2•
የአላህን ስም ስናወሳ “بِسْمِ الله” በማለት እንደሆነ;
-. ይህን ማለት ረስቶ መሀል ላይ ያስታወሰ “بِسْمِ اللهِ فِي أَوَّلِهِ وأَخِرِهِ” ማለት እንደሚችል የመጣ ዘገባ አለ።
3•
በቀኝ እጅ መመገብ/መጠጣት እንዳለብን
4•
ከፊትለፊታችን ካለው መመገብ እንዳለብን;
-. ይሄ አንድ አይነት ምግብ የምንመገብ ከሆነ ነው፤ የተለያየ ምግብ ከሆነ ችግር የለውም።
5•
ስጨርስ ጣታችንን መላስ እንዳለብን;
-. እንደ ወላጅ እና ልጅ፤ ባልና ሚስት አንዳቸው የአንዳቸውን ጣት ማስላስ ሱና መሆኑን የሚጠቁም ሐዲስ አለ።
“الْحَمْدُ للهِ”
•6
ማለት እንዳለብን
-. ሌሎች ምግብ ሲጠናቀቅ የሚባሉ ዚክሮችንም ማለት ይቻላል።
https://t.me/fawaid_00

