ታላቁ ተዓምር
የጨረቃ መከፈል ተዓምር እዚህች ምድር ላይ ከተፈጠሩ ትላልቅ ክስተቶች ውስጥ አንዱ ነው፣ ከብዙ ክፍለዘመናት በፊት ነበር አምላክ በዐረብ ምድር ታላቅ ነቢይን ያስነሳው። ከፊሎች ተከተሉት ብዙዎች ደግሞ አስተባበሉት፣ ታድያስ አንድ ቀን አንተ ሰው ሆይ እውነት እንደምትለው የአምላክ መልዕክተኛ ከሆንክ ተዓምር አሳየን አሉት፣ እሳቸውም በተጠየቁት መሰረት ግዙፏን ጨረቃ ለሁለት በመክፈል ድንቅ ተዓምር አሳዩ። ይህ ተዓምር ጠንካራ ታሪካዊ ማስረጃ ያለው ሙተዋቲር ዘገባ ነው። በወቅቱ እጅግ ብዙ ህዝብ በዐይን-ብረቱ ተመልክቶታል፣ ትዕይንቱን እዚያ ስፍራ ላይ በመገኘት ያስተላለፉልን የዐይን ምስክሮች (Eye witness) ከ20 በላይ ናቸው፣ ከእነርሱ ውስጥ ኢብኑ መስዑድ፣ አነስ ኢብኑ ማሊክ፣ አሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ፣ ኢብኑ ዐባስ፣ ጃቢር ኢብኑ ሙጥዒም፣ ኢብኑ ዑመር ይጠቀሳሉ። ሁሉም እዚያች ቦታ ላይ ከነቢዩ ጋር የነበሩ የዐይን ምስክሮች ሲሆኑ ዘገባውንም ያስተላለፉት በተለያየ ሰነድ ነው። እስኪ ሐዲሶቹን እንመልከት:-
أَنَّ أَهْلَ مَكَّةَ سَأَلُوا رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنْ يُرِيَهُمْ آيَةً، فَأَرَاهُمُ انْشِقَاقَ الْقَمَرِ.
የመካ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ተዓምር እንዲያሳዩአቸው ጠየቁት፣ እሳቸውም ጨረቃን ለሁለት በመክፈል አሳያቸው።
(📚ሶሂህ ቡኻሪ መጽሐፍ 61 ሐዲስ 141)
انْشَقَّ الْقَمَرُ عَلَى عَهْدِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم حَتَّى صَارَ فِرْقَتَيْنِ عَلَى هَذَا الْجَبَلِ وَعَلَى هَذَا الْجَبَلِ فَقَالُوا سَحَرَنَا مُحَمَّدٌ فَقَالَ بَعْضُهُمْ لَئِنْ كَانَ سَحَرَنَا مَا يَسْتَطِيعُ أَنْ يَسْحَرَ النَّاسَ كُلَّهُمْ
በነቢዩ እጅ ጨረቃ በዚህ እና በዚያ ተራራ ላይ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተሰንጥቃ ታየች፣ ቁረይሾችም ‟ነቢዩ በእኛ ላይ አስደግሞብን ነው” አሉ፣ ከፊሎቹ ደግሞ ‟በእኛ ላይ አስደግሞብን ከሆነ ሁሉም ሰው ላይ ማስደገም አይቻለውም” አሉ።
(📚ጃሚዕ አት-ትርሚዚ መጽሐፍ 47 ሐዲስ 341)
انشقَّ القمرُ بمكةَ حتى صار فرقتَينِ فقال كفارُ قريشٍ لأهلِ مكةَ هذا سحرٌ سحرَكم به ابنُ أبي كبشةَ انظروا السُّفَّار فإن كانوا رأوا ما رأيتُم فقد صدق وإن كانوا لم يرَوا مثلَ ما رأيتُم فهو سِحرٌ سحركم به قال فسُئل ا السُّفَّارُ قال وقدِموا من كل وِجهةٍ فقالوا رأَينا.
በመካ ጨረቃ ሁለት እስክትሆን ድረስ ተከፈለች፣ የቁረይሽ ካFiሮች ለመካ ነዋሪዎች ❝ይህ ኢብኑ አቢ ከበሻ (ሙሐመድ) ያስደገመባችሁ ድግምት ነው፣ ከውጪ የሚመጡትን ተጓዢዎች ስለ ነገሩ ጠይቁአቸው፣ እናንተ የተመለከችሁን ነገር እነርሱም ከተመለከቱ በእርግጥም እውነት ነው፣ ያልተመለከቱ ከሆነ ደግሞ ድግምት ነው❞ አሏቸው። ከዚያም ከሁሉም አቅጣጫ የመጡትን ተጓዦች ጠየቁ እነርሱም ‟አዎ አይተናል” ብለው መሰከሩ።
(📚አል-ቢዳያ ወኒሃያ ከኢብኑ ከሢር 3/119)
ይህን ትልቅ ክስተት በወቅቱ ከሁሉም አቅጣጫ የኖሩት ሰዎች ታድመዋል፣ የመካ ጣዖት አምላኪያን ነገሩን ማመን ከብዷቸው ከዐረቢያን ምድር ውጪ ከሚመጡት ስደተኞች እና ነጋዴዎች ማረጋገጥ ችለዋል። ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የጨረቃዋን መከፈል አይተው ነገሩን በማጣራት እስልምና የተቀበሉ ሰዎች ነበሩ። ከእነርሱ ውስጥ በዚያው ወቅት በህንድ የማላባር ንጉስ የሆነው ቻክረዋቲ ፋርማስ ይህን ድንቅ ተዓምር በተመለከተ ጊዜ ስለ ጉዳዩ ከስደተኞች እና ተጓዦች ካጣራ ቡኋለ ልጁን ወደ ነቢዩ በመላክ በልጁ በኩል ከነቢዩ ጋር እንደተገኘ እና ቡኋለ ላይ እራሱ ሄዶ እስልምናን እንደተቀበለ ጥንታዊያን የሆኑ የእጅ-ፁሑፎች ይናገራሉ (manuscript, India Office Library, London, reference number: Arabic, 2807,152-173)«ምንጭ»
ይህን ተዓምር ለማስተባበል የሚሞክሩ አንዳንድ የዋህ ሰባኪዎች ሳያጣሩ የብራድ ቤሊን የቆየ ምርምር (Old research) ያቀርባሉ። ይህ ሳይንቲስት በሰኔ 21, 2010 (GC) ላይ ስለ ጨረቃ መከፈል በተጠየቀ ጊዜ ❝ጨረቃ ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆነ ቦታዎች መከፈሏን የሚያሳይ ወቅታዊ መረጃ የለም❞ /...No current scientific evidence reports that the Moon was split into two or more parts.../ ማለቱ ይታወቃል፣ ልብ በሉ ይህ ሰው በፍፁም ጨረቃ ለሁለት አልተከፈለችም የሚል ነገር አልተናገረም ይልቁኑ በተጠየቀበት ወቅት ምንም አይነት ሳይንሳዊ መረጃ አለመኖሩን ብቻ ነው የጠቀሰው፣ በዚያ ሰዓት መረጃ አልተገኘም (አልተደረሰበትም) ማለት ጨረቃ አልተከፈለም ማለት አይደለም። ከዚያ ቡኋለ የመጡት አዳዲስ ሳይንሳዊ ጥናቶች እንደሚገልጹት ጨረቃ Split/crack መሆኗን የሚያሳዩ ብዙ ፎቶዎች በNational Aeronautics and Space Administration (Nasa) ይፋ ሆነዋል። በስሚዝሶኒያን ብሔራዊ አየር እና ህዋ ሙዚየም የምድር እና የፕላኔቶች ጥናት ማዕከል ከፍተኛ ሳይንቲስት የሆነው ቶም ወተርሰንም በተመሳሳይ ስለ ጨረቃ ስንጥቆች ተጽዕኖ መናገሩ ይታወሳል። የጨረቃ መሰንጠቅ ከዐይን ምስክሮችና ታሪካዊ ሰነዶች በተጨማሪ ሳይንሳዊ እውነታ ያለው ሐቅ ነው። እውን ለአንድ ሐሰተኛ ነቢይ እንዲህ ያለ ተዓምር ሊሰጠው ይችላልን ? ሕሊና ይመልስ።
----------------------------------------------
® Sαlαh responds ✍️