👉መጋኛ መቶኝ ነዉ!
- መቼም በአካባቢያችን መጋኛ መታኝ ተብለን ብዙ ጊዜ ሰምተን ይሆናል : በአንድ በኩል የሚከሰት የፊት መዞር/መድከም በተለምዶ "መጋኛ መታኝ" በሳይንሱ ደሞ facial nerve palsy በመባል ይታወቃል::
-ከ70% በላይ የሚሆነዉ ምክንያቱ ሳይታወቅ ይከሰታል : ይሄም idiopathic facial nerve palsy/Bells palsy ተብሎ ይጠራል::
👉 idiopathic facial nerve palsy/bells palsy ምንድን ነዉ? እንዴትስ ይከሰታል?
-Bells palsy ማለት በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰት የነርቭ (facial nerve) መድከም ሲሆን በአንድ በኩል አይን እንዳይከደን እንዲሁም አፍን ጎትቶ ሊያዞር ይችላል::
-የሚከሰቱበት ምክንያቶች:- ብዙዎቹ መንስኤቸዉ ባይታወቅም
-ኢንፌክሽን ሲሆን በቫይረስ ወይም በባክቴሪያ ሊከሰት ይቻላል:: (HSV-1, EBV, VZV, Mumps, Lyme)
👉ይሄ ህመም ፆታ አይለይም: በእድሜም ህፃናትንም አዋቂንም ያጠቃል::
👉ከሌሎች ተመሳሳይ ህመሞች ልክ እንደስትሮክ (stroke) ካሉ እንዴት መለየት እንችላለን?
-ድንገተኛ መንስኤ (sudden onset) አለዉ
-በአንድ በኩል በግራ ወይም በቀኝ ብቻ (unilateral involvement) ይኖረዋል
-የእግር ወይም እጅ መስነፍ አይኖርም
-ሽፍታ: ሙቀት: ሳል (systemic signs) የመሳሰሉትን አንጠብቅም::
👉ለምርመራ ሀኪሙ መሰረታዊ የሆኑ የላቦራቶሪ ምርመራዎች ሊያዝ ይችላል: እንዳስፈላጊነቱ የCT/MRI ምርመራዎች ሊያስፈልግ ይችላል::
👉ህክምናዉ ለመክደን አስቸጋሪ የሆነዉን ዓይን በሚንከባከቡ የዓይን ጠብታዎች: እንዲሁም በመኝታ ጊዜ ዓይንን መሸፈንን ጨምሮ ጥቂት ቀናት የሚወሰዱ መድሃኒቶች ሊታዘዙልን ይችላሉ::
👉ህክምናዉ በጊዜ ሆስፒታል መሄድን ይፈልጋል:: ባህላዊ ወይም ሀይማኖታዊ መፍትሄን ፍለጋ መዘግዬት የህክምናዉን ዉጤታማነት ይቀንሳል::
👉ፀበል ወይም ፀሎትን ከህክምናዉ ጎን ለጎን ማድረግ ይቻላል::
👉ከህክምና በኃላ የሚኖረዉ ለዉጥ ህመሙ ሲከሰት ባለዉ ቅርጽ እና በብዙ ምክንያቶች የሚወሰን ሆኖ አብዛኛዉን ጊዜ በተለይ ደሞ ልጆች ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ በሚል ደረጃ የማገገም እድላቸዉ ከፍ ያለ ነዉ::
ዶ/ር ሀብታሙ ስሜነህ - የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስት
Dr Habtamu Semeneh - pediatrician
Disclaimer: This post is for teaching, not for treatment
ለማህበረሰባችን እዉቅና ለመፍጠር ብቻ የተዘጋጀ
@HakimEthio
29August 31, 2026 4.5K 15


