የህክምና ትምህርት እና ህክምና ሙያ የህክምና ተማሪ በትምህርት ሂደት ውስጥ በብዙ አስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ… — Hakim — TG.ME

የህክምና ትምህርት እና ህክምና ሙያ

የህክምና ተማሪ በትምህርት ሂደት ውስጥ በብዙ አስቸጋሪ ፈተናዎች ውስጥ ያልፋል!

1: እዛ ቦታ ለመድረስ ያለፈበት ስኬታማ የትምህርት ቆይታ የሚፈጥረው EGO እና ለፈተናዎች ለአቅም ማጣቶች ለመውደቅ መነሳቶች react ሚያደርግበት መንገድ ልክ ያለመሆን

2: የትምህርቱ አሰልቺነትና አድካሚነት እንዲሁም ለረጅም አመታት እጅግ stressful environment ውስጥ መቆየቱ በዚህ ላይ ደግሞ ማንኛውም የuniversity ተማሪ እንደሚገጥመው ሁሉ ከቤተሰብ ርቆ የመማር ፈተና በግቢ ካፌ የምግብ አለመስማማት የአካባቢው አለመረጋጋት ጨምሮ ሌሎችም ፈተናዎች የህክምና ትምህርት ፈተናዎች ላይ ይደመራሉ!

3: የቤተሰብም የሚገባው ተማሪም ሙያውን እንጂ የህክምና ትምህርት ላይ ያለው awareness ዝቅተኛ መሆን

እንዲሁም በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ተማሪዎች ፍላጎታቸው እምብዛም ቢሆንም እንኳ በቤተሰብም በማህበረሰብም ግፊት ወደ ህክምና ትምህርት መግባት

4: ሌሎች talent ያላቸው ተማሪዎችም talentታቸውን ለማውጣት የትምህርቱ ትንፋሽ ማሳጣት ከተሰጧቸው ተሰጥኦዎች እንዲለያዩና እንዲቀብሩት ማድረጉ

በተለይም ከረጅም አመታት እልህ አስጨራሽ የህክምና ትምህርት መጠናቀቅ በኃላም በሙያው የሚገኘው ደሞዝ ከወቅታዊ የኑሮ ሁኔታ ጋር ተመጣጣኝ አለመሆን ጉዳዩን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አድርጎታል!

ብቻ ብዙ ማለት ይቻላል እናንተም ሀሳብ ስጡበት

በመጨረሻም... we are more than proud to be a doctor!

Watch my podcast: https://youtu.be/is9tolyZ6Xo?si=KNvLSO1Vxe-SHbEC

Dr. Rediet Moges (DocArt)

@HakimEthio
❤48👍1
September 1, 2026 4.3K 5