ወንጀላችን በበዛ ቁጥር የሸይጧን ምርኮኛ እንሆናለን። ከወንጀል አደጋ ደግሞ ሁሌም የሸይጧን ምርኮ ውስጥ… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

ወንጀላችን በበዛ ቁጥር የሸይጧን ምርኮኛ እንሆናለን። ከወንጀል አደጋ ደግሞ ሁሌም የሸይጧን ምርኮ ውስጥ መሆንህ፣ በዝንባሌህ እስር ቤት መግባትህና በስሜትህ ሰንሰለት መታሰርህ ነው።

​በጠላት እንደተማረከ ሰው አስከፊ ሁኔታ ላይ ያለ፣ ዝንባሌን እንደመከተል ጠባብ እስር ቤት የገባና በስሜት ሰንሰለት እንደመታሰር የከበደ አደጋ የለም።

​በእንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ያለ ሰው እንዴት ነው ወደ አላህና ወደ ሚቀጥለው ሀገር የሚያቀርበውን ስራ የሚሰራው? በሸይጧን ተማርኮ፣ በዝንባሌው ታስሮ፣ በስሜቱ ታስሮ ሳለ።


አላህ ካለንበት ጨለማ ያውጣን።


𝐀𝐌𝐈𝐍.. ❤️‍🩹
❤30👍11
September 5, 2026 1.8K 6 1