በአማካይ አንድ ሰው 80 አመት ቢኖር... ይህ ማለት 960 ወራት ብቻ ነው ያለን። ወይም 4,160 ሳምንታት… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

በአማካይ አንድ ሰው 80 አመት ቢኖር...

ይህ ማለት 960 ወራት ብቻ ነው ያለን።
 ወይም 4,160 ሳምንታት ብቻ።

እስኪ ቆም ብለህ አስብ..

የህይወትህ "ባትሪ" 🔋 ያለው 4,160 ሳምንታት ብቻ ነው።

አሁን እድሜህ 30 ከሆነ፣ 1,560 ሳምንታትህ አልቋል! ቀሪው 2,600 ብቻ ነው።

እድሜህ 25 ከሆነ፣ 1,300 ሳምንታትህ ተቃጥሏል! ቀሪው 2,860 ነው።

ጨዋታው ይሄ ነው፡ እያንዳንዱ ሳምንት አንድ 'Block' ነው

አስበው፣ የህይወትህን ሳምንታት በሙሉ በወረቀት ላይ እንደ ትናንሽ ሳጥኖች ብትስላቸው።ከዛ እያንዳንዱ ያለፉት ሳምንታቶችህ በጥቁር ቀለም ቢቀቡና ያንን ምስል ብትመለከተው፣ ምን ይሰማሃል?

ምን ያህል ብዙ ሳጥኖች በጥቁር እንደተቀቡ ስታይ ትደነግጣለህ።

ምን ያህል ትንሽ ነጭ ሳጥኖች እንደቀሩህ ስታይ ትፈራለህ።

ይህ ፍርሃት ግን ጥሩ ነው!

ምክንያቱም እያንዳንዱ የቀረህ ነጭ ሳጥን ምን ያህል ውድ እንደሆነ እንድትረዳ ያደርግሃል!

ለቀጣዩ አንድ ሳምንት፣ ይህንን አንድ ጥያቄ እራስህን ጠይቅ፦

"ይህ ሳምንት በህይወቴ ታሪክ ውስጥ ቢፃፍ፣ ርዕሱ ምን ይሆን ነበር?"

ስለ ቢዝነሴ ያቀድኩበት ሳምንት?

በከንቱ ጭንቀት ያሳለፍኩት ሳምንት?

"ከምወዳቸው ሰዎች ጋር ጊዜ ያሳለፍኩበት ሳምንት"

"ቲክቶክ ላይ Scroll እያረኩ ያባከንኩት ሳምንት"?


ይህንን  ጥያቄ ስትጠይቅ፣ ጊዜን እንደ ገንዘብ ማየት ትጀምራለህ።

እያንዳንዱን ቀን በዕቅድ ትኖራለህ።

ለማይጠቅሙ ነገሮች ጊዜህን መግደል ታቆማለህ

የቀሩህን ነጭ ሳጥኖች፣ በህይወትህ ውስጥ ምርጥ በሆኑት ታሪኮች ትሞላቸዋለህ።

ጊዜህን እየገደልክ ነው ወይስ ኢንቨስት እያደረክበት ነው?
❤‍🔥14❤10🔥4😨4
August 29, 2026 2.3K 13 19