ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 245❵ #hadith245 "ኢብኑ አብባስ (ረ አ) እንዲህ ሲሉ… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 244❵ #hadith244 "አቡ ሁረይራ (ረ አ) እንዳስተላለፉት የአላህመልእክተኛ (ሰ አ ወ) እንዲህ ብለዋል ።በራሱ በልጁናበገንዘቡ በኩል በሙእሚን ላይ መከራዎች ከመውረድአይቦዝኑም ከወንጀል የፀዳ ሆኖ አላህነ እሲኪገናኝ ድረስ። (ተርሚዝ ዘግበውታል ሀዲሱን ሶሂህ ብለውታል ) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/17316 🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ…
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 245❵ #hadith245

"ኢብኑ አብባስ (ረ አ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል።ኡየይነህ ኢብኑ ሂስን (ረ አ) ወደ መዲና በመምጣትከወንድሙ ልጅ ከሁር ኢብኑ ወይስ ዘንድ አረፈ ። ሁርኡመር (ረ አ) ከሚያቀርባቸው ሰዎች አንዱ ነበር ።የቁርአንን መልእክት የመረዳት የበለጠ ችሎታ ያላቸውሰዎች ወጣቶችም ይሁኑ ሽማግሌዎች ሰዎችም የኡመር(ረ አ) ችሎት አባላትና አማካረከዎች ነበሩ ። የወንድሜንልጅ ሆይ በዚህ አዛኝ መሪ ዘንድ ተደማጭነት ያለህ ሰውነህና ከፊቱ መቅረብ እችል ዘንድ ፈቃድ ጠይቅልኝበማለት ኡየይነህ የወንድሙን ልጅ ይጠይቃል ።ፈቃድጠየቀለት ኡመር (ረ አ) ፈቀዱለት ።ኡመር ዘንድ በቀረበጊዜ በአላህ እምላለሁ ከኸጣብ ልጅ በርከት ያለ ስጦታአትሰጠንም በፍትህ በፍትህ አትፈርድልንም በማለትተናገሩ። ኡመር (ረ አ) አለ ቅጥ ተቆጡ ሊቀጡትእስኪከጅሉ ድረስ ። ሁር እንዲህ አላቸው ።የሙእሚኖችአሚር ሆይ አላህ ለነብዮ (ሶ አ ወ) ገርን ጠባይ ያዝበመልካም እዘዝ ባለጌዎችም ተወዋቸው ብሏቸዋል።ይህ ሰው ደግሞ ከባሌጌዎች አንዱ ነው ።ሁር ይህንንየቁርአን አንቀፅ ባነበበ ወቅት ኡመር ቁጣቸው በረደ።ኡመር (ረ አ) የአላህ መፅሀፍ (መመሪያ) ቅንጣት የማይተላለፍ ሰው ነበሩ።

(ቡኻሪ ዘግበውታል )



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17337

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
🥰7❤4
July 13, 2026 2.4K 4