ስቃይ የራሱ የሆነ ውበት አለው
ህይወት ከኤልያስ በቃኝ! ጩኸት ጀርባ ከዳዊት ነፍሴ ሆይ ለምን ትጨነቂያለሽ? ፍንዳታ በስተጀርባ እና ከኤርምያስ የውልደት ቀን እርግማን ጀርባ አንድ እውነት አለ እሱም ሰው መሆን መታመም ነው።🖤
ቅዱስ ጳውሎስ ህይወቱን እስኪጠላ ድረስ የተጨነቀበት አሳፍ ልቤን በንጽህና መጠበቄ ከንቱ ነው ብሎ የደከመበት እና ሙሴ እባክህ ግደለኝ ብሎ የለመነበት ያ ጊዜ ምክንያቱ ቢለያይም በእኔና እናተ አሁንም ምንጮከው💔ምናሳልፈው ቅፅበት
እያንዳንዳችንን በየግላችን የሚጎበኝበት ስውር ሰዓት አለው ።እዮብ በተስፋ መቁረጥ አመድ ላይ ተቀምጦ ለምን አልጠፋሁም?ሲል🥹 ዕንባቆም ደግሞ ወደ ሰማይ እያየ እስከ መቼ? ብሎ ሲጠይቅ የሰው ልጅ የስቃይ ጥልቀት ገደብ አልባ መሆኑን እንረዳለን።በቃ ይሄ እሚኖር ኡነት ነው።
መጽሐፍ ቅዱስ ጠንካራና ፍጹም የሆኑ ሰዎችን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የተሰበሩ የደከሙና ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን ስቃይም ጭምር በግልጽ ያስቀመጠው ያለምክንያት አይደለም።ነፍስ ከመጠገኗ በፊት መሰበር ከመድፈርዋ በፊት መሸበር ከመጽናናቷም በፊት መሪር ዕንባን ማፍሰስ አለባት በቃ🎧ህመሙ ያማል🥹 ግን ያጠነክራል🤌
ስቃይ የራሱ የሆነ ውበት አለው ልብህ ሳይሰበር ሕይወትን በትክክለኛ መነጽር ማየት አትችልም🖤ከዚህ ከተሰበረው ፍርስራሽ ውስጥ ነው ማንም ሊያፈርሰው የማይችል አዲስ የነፍስ ጥንካሬ የሚገነባው🔪🕊
እግዚአብሔር 🤍ከተሰበረ ልብ ይልቅ የሚወደው ሌላ ማደሪያ የለውምና ጨለማዬ አብቅቶ ስብራቴ አዲስ ውበት ሆኖ የህመሜ የማጌጥበት ቀን ቅርብ ነው።