በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ ሳንስማማ አንፈርምም - ተመካካሪዎች
አዲስአበባ የኦሮሚያ ክልል መቀጫ ትሁን የሚለው አማራጭ በግድ በቃለ ጉባኤ ላይ እንዲካተት መደረጉን ምንጮች ተናግረዋል።
ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አራት የሥራ ቡድኖች ተጠናቅረው በቀረቡ የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ዙሪያ መግባባት ላይ መድረሳቸውን በተዘጋጁ የቃለ ጉባኤ ሰነዶች ላይ በመፈረም አረጋግጠዋል ቢልም፤ በአራቱ የሥራ ቡድኖች ውስጥ የሚገኙ “በርካታ” ተመካካሪዎች በቃለ ጉባኤዎቹ ላይ አለመፈረማቸው ተሰምቷል።
በምክክር ሂደቱ ከፍተኛ መነጋገሪያ የሆነው የፌደራል ከተሞች ጉዳይ አጀንዳ ላይ ከስምምነት ሳይደረስ በቃለ ጉባኤ ላይ አንፈርምም ያሉ ተመካካሪዎች በርካታ መሆናቸውን የገለጡልን ምንጮች፤ ቃለ ጉባኤ ባልሰፈረበት ባዶ መዝገብ ላይ ፈርሙ የተባሉ ሌሎች ተመካካሪዎችም “በባዶ መዝገብ ላይ አንፈርምም” በሚል ለቃለ ጉባኤ መመዝገቢያ በተዘጋጀው ቅጽ ላይ ሳይፈርሙ መቅረታቸውን ተናግረዋል።
ኮሚሽኑ ለተመካካሪዎች ባቀረበው “የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓት” ሰነድ መሰረት፣ በሥራ ቡድን ደረጃ የውሳኔ ስምምነት አለ ለማለት የተመካካሪዎችን 75 በመቶ ድጋፍ ማግኘት ያስፈልጋል። በማንኛውም የምክክር ደረጃ ውሳኔ የሚሻ ጉዳይ ላይ ውሳኔ ለማስተላለፍ ደግሞ ቢያንስ 75 በመቶ ተመካካሪዎች መገኘት እንዳለባቸውም ሰነዱ ያመላክታል።
ይሁንና ኮሚሽኑ ስምምነት ላይ ተደርሷል ሲል ይፋ ባደረገባቸው የሥራ ቡድኖች፣ ሁለቱም ቅድመ ሁኔታዎች መሟላታቸው በቆጠራ አለመረጋገጡን፣ የምክክር ሂደቱን የሚመሩ የኮሚሽኑ ባለሙያዎችና የምክረ ሀሳብ አጠናቃሪ ቡድን አባላትም ስለ ቅድመ ሁኔታው አለማንሳታቸውን ምንጮች ገልፀዋል።
የፌደራል ከተሞች ጉዳይን እየተመካከረበት የሚገኘው የሥራ ቡድን 7፣ የምክክር ሂደቱን አጠናቅቋል በሚል ቃለ ጉባኤ ላይ እንዲፈረም መወሰኑን