የዮሴፍ እና የወንድሞቹ ፍጻሜ ለምን ተለያዬ?
ዮሴፍ እና ወንድሞቹ [ቤተ-ሰቦቹ] ወደ ግብፅ የገቡበት መንገድ [ምክንያት] ይለያያል። ዮሴፍ ተሽጦ፣ እነርሱ ተቸግረው። ዮሴፍ እንደ ባሪያ፣ እነርሱ እንደ ነጋዴ። ርሱ ተገዝቶ፣ እነርሱ እህል ሊገዙ። ዮሴፍ ተገዶ፣ ወንድሞቹ ወደው።
ዮሴፍ ወደ ግብፅ ባሪያ ሆኖ ቢገባም፣ ገዥ [ለመፍትሒ የሚፈለግ ሰው] ሆኖ ኖሯል። ወንድሞቹ በዮሴፍ ምክንያት ለጊዜው ቢከበሩም፣ ከርሱ መሞት በኋላ በግብፅ ባሪያዎች ሆነዋል። ለ430 ዓመታት ያህል አስከፊ የባርነት ጊዜ አሳልፈዋል።
የዮሴፍን መሸጥ ሦስት ውጤቶች አምጥቷል። 1) ዮሴፍን ራእይ አካል አስይዟል። (ለራሱ) 2) ቤተ-ሰቡን ከራብ አድኗል። (ለቤተ-ሰቡ) 3) የግብፅን ሕዝብ ከራብ አትርፏል። (አስተዳደራዊ መፍትሔ)
የዮሴፍ እና የወንድሞቹ ፍጻሜ ለምን ተለያዬ?
ምናልባት ወንድሞቹ የዘሩትን አጭደው ይሆን? በሁለቱ መካከል ልዩነት ያመጣው፣ ራእይ እና ምልልስ ይሆናል። ዮሴፍ የሆነውን የሆነው በተቀበለው ራእይ፣ በአምላኩ ሞገስ እና በንጹሕ ምልልሱ ምክንያት ነበረ።
11
7January 10, 2025 3.1K 6