Grace Commission: post #2110 — TG.ME

#መንገዳችን ይለያያል!

ዮሴፍና ሙሴ ወደ ቤተ መንግሥት የገቡበት መንገድ ይለያያል። ዮሴፍ ሕልም ፈትቶ [ምክረ ሐሳብ አቅርቦ] ሲሆን ሙሴ ግን በንጉሡ ሴት ልጅ ፊት ምገስ አግኝቶ ነው። ዮሴፍ በሌላ ስፍራ ተሠራ፥ ሙሴ በቤተ መንግሥት እየተሠራ አደገ። ዮሴፍ በግብፅ ነግሷል። ሙሴ ግን ቤተ መንግሥቱን ትቶ ሄዷል። ዮሴፍ በግብፅ መንገሡ፣ ሙሴም ንግሥናን መተዉ ሁለቱም ግብ ነበረው። የዮሴፍ መንገሥ፣ በዋናነት ለግብፃውያን ነበረ። የሙሴ ንግሥናን መተው ደግሞ ለእስራኤላውያን ነጻ መውጣት ነበረ።

የሁላችንም መንገድ የግድ አንድ ዐይነት መሆን አይጠበቅበትም። ዋናው ነገር፣ ኑሯችን የመለኮት ዐላማና ቅኝት ይኑረው!
❤26👍9🔥2
January 6, 2025 2.9K 17