Grace Commission: post #2090 — TG.ME

ኢየሱስን #ከእምነት #ተቋምህ በላይ ትወደዋለህ?

ምንአልባት ኦርቶዶክስ ትሆናለህ፤ ከኦርቶዶክስ ሃይማኖት በላይ፣ ኢየሱስን ትወደዋለህ?

ካቶሊክም ከሆንህ፣ ከእምነትህ ተቋም በላይ ኢየሱስን ትወደዋለህ?

ወንጌል አማኝም ከሆንህ፣ ኅብረት ከምታደርግበት አጥቢያ በላይ ኢየሱስን ትወደዋለህ?

አንዳንድ ሰዎች ከኢየሱስ ይልቅ ለሃይማኖታቸው ከፍ ያለ ቅናት አላቸው። ለዚያም ነው ኢየሱስን ትተው #ተቋም #ለማስቀጠል ሁሉንም ዋጋ የሚከፍሉት።

እንደ እግዚአብሔር ቃል የታነጹ ተቋማት፣ እጅግ በጣም ያስፈልጋሉ። በልባችን የኢየሱስን ያህል ስፍራ ግን አይገባቸውም። #የትኛውም #ነገር ለኢየሱስ ያለንን ''ንጽሕና እና ቅንነት" ከለወጠ ከእግዚአብሔር አይደለም!

#ኢየሱስ ከተቋማቱ በፊት ነበረ!
የእኛ ጌታ #ከተቋማቱ በኋላም ይኖራል!
❤15👏5👍4🔥1🥰1
November 26, 2024 2.7K 7