እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል" 🙏 ✨ ጥላ የሆነው ዘጸአት የግብጽን በኩር ገድሎ የህዝቡን… — ክርስቲያን ነኝ️️️ — TG.ME

🙏 "እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል" 🙏 ✨ ጥላ የሆነው ዘጸአት የግብጽን በኩር ገድሎ የህዝቡን ከባርነት ነጻ መውጣት እና መላቀቅ አበሰረ! 💠 “... በግብፅ አገር በእስራኤል ልጆች ቤቶች ላይ አልፎ ግብፃዊያንን በመታ ጊዜ፥ #ቤቶቻችንን_ያዳነ #የእግዚአብሔር_የማለፉ_መሥዋዕት...” (ዘጸአት 12፥27) ብለው የሚጠሩትን የፋሲካ በግ አረዱ። ✨ የጥላው እውነተኛ አካል የሚገለጥበት ጊዜ ሲመጣ ደግሞ፣ እኛን የግብፅ ምሳሌ በሆነው ኅጢአተኝነት ውስጥ አሰኘን፣ በዚህን ወቅት እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር ከእኛ በሆነ በግ ወይንም ሌላ ነገር ሳይሆን የእራሱ የሆነው በኩር ልጁን ለሐጢአታችን መስዋዕት አድርጎ በማቅረብ ከራሱ ጋር አስታረቀን! 💠 “... ገና ኀጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞተ፤ ይህም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያሳያል።” (ሮሜ 5፥8) ✨ ደስ ይበላችሁ #ኢየሱስ_የዘላለም_ቤዛችን_ነው! ✨ 🔑 #የምስራች:- ኢየሱስ ክርስቶስ ለሐጢያታችን በመሞቱ #ከእግዚአብሔር_ቁጣ_ለዘላለም_ድነናል! #እርሱ: ቤቶቻችንን ያዳነ የእግዚአብሔር የማለፉ መሥዋዕት ነው! 🔴 ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶልናል! 🔴 ከእግዚአብሔር ጋር በእራሱ መስዋዕት ታርቀናል! 🔴 ኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ጊዜ ራሱን መስዋዕት አድርጎ አሳልፎ በመስጠቱ እኛ ለዘለዓለም ጸድቀናል! ✨ ይህ ቀን: #የሐጢያት_ትክክለኛው_መስዋዕት የተገኘበት እና የተከፈለበት ነው። 🔴 ፋሲካ የታረደው የበጉ መጠሪያ ነውና እንኳን ለጌታችን ለመድሐኒታችን የፋሲካ በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሳችሁ! የሕያው እግዚአብሔር ቤተሰብ ቤተክርስቲያን ነቢይ ዳዊት አለሙ! 10-08-2017

April 17, 2025 311