ሆያ ሆዬ
ሆያ ሆዬ /4/
እዛ ማዶ ሆ
ምን ይታያል
ታቦር ተራራ
ብርሃን ለብሷል
ጌታ ቀሚሱ
ያንፀባርቃል
በክብር ውበት
በግርማው ቆሟል
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
ጴጥሮስ በግርማ ሆ
እጅግ ደንግጦ
መሬት ወደቀ
እራሱን ስቶ
ኤልያስ ሙሴ
መጡ ከፊቱ
የእግዚአብሔርን ልጅ
ኑ ተመልከቱ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
አብ በሰማያት ሆ
ድምፁን አሰማ
ልጁን እንመን
እርሱን እንስማ
በፍቅር ብርሀን
እንዲያደምቀን
እንቅረብ ፊቱ
ስሙን አውቀን
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
ከደብረ ፅዮን ሆ
ህዝቡን ይጠራል
በዚህ በግርማው
ዳግም ይመጣል
ከሙሴ ጋራ
ከኤልያስ
ሊያቆመን ቀኙ
እኛን በነፍስ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
የሙሴን ጌታ ሆ
ሙሴ ነው ሲሉ
እንደ ኤልያስ
ነቢይ እያሉ
አይሁድ ቢስቱ
ቢነሱበት
ኤልያስ ሙሴ
መሰከሩለት
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
ሆያ ሆዬ /4/
የአመት ልምዳችን ሆ
ከጥንት የመጣ
የቡሄ ለታ
ችቦ ሲወጣ
ከእማምዬ ቤት
ሙልሙሉ ይምጣ
ሆያ ሆዬ በሉ ክርስቲያኖች በሙሉ /2/
አመት አውደዓመት ድገምና አመት ድገምና /2/
የአባብዬን ቤት " "
ሰላም ይሙላበት
የእማምዬን ቤት
ፍቅር ይሙላበት
ክበር በንስሐ ክበር በፀሎት የነአባብዬን ቤት ጌታ ይግባበት
ክበር በንስሐ ክበር በፀሎት የነእማምዬን ቤት ጌታ ይግባበት
4August 13, 2026 1.1K 11