#MoE
✔️ በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና 563 ሺ 960 ተማሪዎች ተመዝግበው 550 ሺ 210 ተማሪዎች ፈተናውን ወስደዋል።
ፈተናውን ከወሰዱት ውስጥ 12.8 በመቶ የሚሆኑት ተማሪዎች 50 በመቶ እና ከዚያ በላይ ማምጣት ችለዋል።
✔️ ዘንድሮ በአጠቃላይ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ማለፍ የቻሉት 70 ሺ 544 ናቸው።
ካለፉት መካከል በተፈጥሮ ሳይንስ 16.5 በመቶ ሲሆኑ በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ 8.33 በመቶ ናቸው።
✔️ ከፍተኛ ውጤት !
በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 591.6 ከ600 ተመዝግቧል። ተማሪው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ ተማሪ ነው።
ከሴት ደግሞ 583 ከ600 ሲሆን ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ነው።
"ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል። " - ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ (የትምህርት ሚኒስትር)
Via: @tikvahethiopia
2
1August 22, 2026 329 2

