📌 የስራ መደብ: የሽያጭ ባለሙያ
💰 ደሞዝ: ወርሃዊ
📂 ልምድ: 0-1 ዓመት
📍 ቦታ: አዲስ አበባ
📅 የማመልከቻ ጊዜ ማብቂያ: ነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
📂 የስራው ዝርዝር:
አማሄ ማኑፋክቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር (AMAHE MANUFACTURING P L C) የማርኬቲንግ፣ የማስተዋወቅ እና የንግድ ማስታወቂያ ሥራዎቻችንን በበላይነት የሚመራ ከፍተኛ ብቃትና ተነሳሽነት ያለው የሽያጭ ባለሙያ አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ተመራጩ አመልካች የሽያጭ ስትራቴጂዎችን የማዘጋጀት፣ ከዋና ዋና ደንበኞች ጋር ጠንካራ ግንኙነት የመስረት፣ የማስተዋወቂያ ዘመቻዎችን የማስተዳደር እና ዘላቂ የንግድ እድገትን ለማረጋገጥ የገበያ ጥናቶችን የማካሄድ ኃላፊነት ይኖርበታል።
• የትምህርት ደረጃ፦ የሰርተፊኬት ደረጃ (Certificate Level)
• የሥራ ልምድ፦ 0 ዓመት (ከ0 - 1 ዓመት ልምድ ያለው/ላት)፤ በማርኬቲንግ ኤጀንሲዎች፣ በማስተዋወቅ ወይም በማስታወቂያ ድርጅቶች ውስጥ በኃላፊነት ደረጃ የሠራ/ች ይበልጥ ይመረጣል።
• የቴክኒክ ብቃት፦ የማርኬቲንግ ስትራቴጂ ዝግጅት፣ የዲጂታል እና ሚዲያ ማስተዋወቂያ (BTL/ATL) እንዲሁም የገበያ ጥናት ትንተና እውቀት።
• ዋና ዋና ክህሎቶች፦ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ማውጣት፣ የውል ድርድር፣ የደንበኞች ግንኙነት አስተዳደር እና የዘመቻ መሪነት ብቃት።
• ዋና ዋና ኃላፊነቶች፦አጠቃላይ የሽያጭ ስትራቴጂዎችን ማዘጋጀት።ከትላልቅ ደንበኞች እና ተቋማት ጋር የንግድ ግንኙነቶችን መፍጠር እና ውሎችን መደራደር።የህዝብ ግንኙነት (PR) እና የማስታወቂያ ዘመቻዎችን በበላይነት መከታተልና ማስተዳደር።የኢንዱስትሪውን እና የተወዳዳሪዎችን ሁኔታ የሚያሳዩ የገበያ ጥናቶችን ማካሄድ።
• የሥራ ሰዓት፦ መደበኛ የሙሉ ጊዜ የሥራ ሰዓት
• ክፍት የሥራ መደብ ብዛት፦ 1 (አንድ)
📩 ዝርዝር መረጃ ለማግኘት እና ኣፕላይ ለማድረግ ይህንን ሊንክ ይጠቀሙ

