ክፍለጦሩ በቀጠናው ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ አበረከተ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ክፍለጦሩ በቀጠናው ለሚገኙ ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ አበረከተ።  

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም

የምዕራብ ዕዝ አብዲሳ አጋ ክፍለጦር በጠገዴ ወረዳ አለም ገነት ከተማ ለሚኖሩ ወላጅ አልባ እና ድጋፍ ለሚሹ ተማሪዎች የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በቦታው ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የክፍለጦሩ የሰው ሀብት አመራር ሃላፊ ሻለቃ እስሉየ ገድሉ፤ የተደረገው ድጋፍ መማር እየቻሉ በኢኮኖሚ /በገንዘብ/ እጥረት ትምህርታቸውን መከታተል ያልቻሉ ተማሪዎች መማር እንዲችሉ በማሰብ መሆኑን ተናግረዋል።

የሠራዊቱን ድጋፍ አስመልክተው አስተያየት የሰጡት የአለም ገነት ከተማ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን በበኩላቸው ሠራዊቱ የሀገራችን ዘላቂ ሰላምና ልማት ዋስትና መሆኑን ገልፀው፤ የትምህርት ዘርፉን መደገፍ አንዱ የሰው ሀብት ልማት ስራ ላይ ትልቅ አቅም የሚፈጥርና ፋይዳው የጎላ ነው ብለዋል።

ድጋፍ ከተደረገላቸው ተማሪዋች መካከል የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ተማሪ ፋኑስ ላቄ በችግር ምክንያት ባለፈው አመት ትምህርቱን አቋርጦ እንደነበር በማስታወስ በዚህ አመት ሠራዊቱ ባደረገለት ሙሉ የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ ያለምንም ችግር ትምህርቱን በትኩረት እንደሚከታተል ገልጿል። 

ዘጋቢ ሀብታሙ የሺጥላ
ፎቶ ግራፍ ወርቅነሽ ተስፋየ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👏17❤12👍2🔥1
September 18, 2026 3.9K 1