ጷግሜ 3 የጽናት ቀን በኮምቦልቻ ከተማ ተከበረ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ጷግሜ 3 የጽናት ቀን በኮምቦልቻ ከተማ ተከበረ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

የጽናት ቀን ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም በኮምቦልቻ ከተማ ሲከበር በዕለቱ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በማውጣትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙር በመዘመር ተከብሯል። በአከባበሩ የ11ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ እና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ፀጥታ መምሪያ በጋራ ተሳትፈዋል።

የ11ኛ ዕዝ ዘመቻ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ደረጀ ግርማ፣ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ጌታቸው ሙህየ እና የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የሠላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ነጋ በዕለቱ የጽናት ቀንን አሥመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጽናት ቀን ስናከብር ጀግኖቻችንን የምንዘክርበት፣ ለሀገር ሰላምና ጸጥታ የሚሠሩ የጸጥታ ኃይሎችን ቅድሚያ በመስጠት የምናከብርበት እና ለሀገር ክብርና ሉዓላዊነት፣ እንዲሁም ለሀገር ሰላምና ልማት በአንድነት ዘብ የምንቆምበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።

የጽናት ቀን አከባበሩ የጀግኖችን ታሪክ በማስታወስ፣ የሀገር ፍቅርን፣ የሀላፊነት ስሜትንና የጋራ ጽናትን በማጠናከር የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታን ለማጠናከር ያለውን ሚና አጉልቷል። ዘገባው የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤9👍6🔥2
September 8, 2026 2K