ክፍለጦሩ ለአቅማ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ክፍለጦሩ ለአቅማ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 02 ቀን 2018 ዓ.ም

በማዕከላዊ ዕዝ የዋልታ ክፍላጦር አዛዥ ኮሎኔል ጌታቸው ወደጄ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አባይ ጮማን ወረዳ ለሚገኙ አቅማ ደካማ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስና ዩኒፎርም አበርክተዋል።

ድጋፉ በአካባቢው በኢኮኖሚ ደካማ ለሆኑ ቤተሰቦች የሚገኙ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ የሚያጋጥማቸውን የቁሳቁስ እጥረት በማቃለል፣ በትምህርታቸው የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ለማበረታታት ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ተመሪዎች የሀገር የነገ ተስፋ መሠረት በመሆናቸው፣ የተቸገሩ ተማሪዎችን መደገፍ የተማሪዎቹን የትምህርት ጉዞ ከማሳለጥ ባለፈ በአካባቢው የትምህርት ተሳትፎን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና አለው ስሉም አዛዡ ተናግረዋል።

የአባይ ጮማን ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሶሪ ፋራዳ ሠራዊቱ ህይዎቱን መስዋዕት አድርጎ ሀገር ከመጠበቅ ባሸገር ለህዝቡ እና ለቀጣይ ትውልድ ተስፋ ስጭ ተግባር በመፈፀሙ ምስጋና አቅርበዋል።

ዘጋቢ ሁሴን ጀማል
ፎቶግራፍ ሃብታሙ ሁሴን

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍23❤14🔥3
September 7, 2026 3.3K 2