ከሠራዊቱ በጡረታ ለሚሰናበቱ አባላት የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ከሠራዊቱ በጡረታ ለሚሰናበቱ አባላት የሽኝት መርሃ ግብር ተካሄደ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጷጉሜ 03 ቀን 2018 ዓ.ም

የሜጀር ጀኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከሠራዊቱ በጡረታ ለሚሰናበቱ አባላት የሽኝት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የኮሌጁ አዛዥ ተወካይ ኮሎኔል ዓለማየሁ ስበቡ ፣ በጡረታ የሚሰናበቱ አባላት ኮሌጁ ለደረሰበት የብቃት ደረጃ መሠረት በመጣል፣ እውቀታቸውንና ጉልበታቸውን ሳይሰስቱ ለተቋሙና ለሀገራቸው ላበረከቱት አስተዋፅኦ ልባዊ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።

አባላቱ ከሠራዊቱ በጡረታ ቢሰናበቱም ከማኅበረሰቡ ጋር በሚኖራቸው ቀጣይ ሕይወት የተቋሙንና የኮሌጁን እሴቶች የሚያስተላልፉ አምባሳደሮች እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልፀዋል።

የኮሌጁ ምክትል አዛዥና የሥልጠና ዲን ኮሎኔል ወልደተክላይ ወልዳይ በበኩላቸው፣ በጡረታ የሚሰናበቱ አባላት በውትድርና ሕይወታቸው የሀገርን ሉዓላዊነትና ሰላም ለመጠበቅ ያደረጉትን አስተዋፅኦ አድንቀው፣ በኮሌጁ በአመራርነትና በተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች ያበረከቱት አስተዋፅኦ ለተቋሙ አቅም ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ መጪውን አዲስ ዓመት አስመልክቶ በሆለታ ከተማ ለሚኖሩ የአቅም ውስንነት ላለባቸውና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማኅበረሰብ ክፍሎች የገንዘብ፣ የአልባሳትና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።

ዘጋቢ ሀይለማርያም ተሾመ
ፎቶግራፍ ጥሩወርቅ አናጋው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤23👍7🔥2
September 8, 2026 1.7K 1