በሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት ሰልጣኞች የትከሻ ምልክት ለበሱ። የኢፌዴሪ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

በሜጀር ጄኔራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የ2ኛ ዓመት ሰልጣኞች የትከሻ ምልክት ለበሱ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 08 ቀን 2019 ዓ.ም

በሜጀር ጀነራል ሙሉጌታ ቡሊ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በተለያዩ የቴክኒክና ሞያ ዘርፎች በመደበኛ ፕሮግራም ስልጠናቸውን እየተከታተሉ ለሚገኙ የሁለተኛ ዓመት ሰልጣኞች የትከሻ ምልክት የማልበስ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ ስነ-ስርዓት ላይም ከኢትዮጵያውያን ሰልጣኞች በተጨማሪ የሩዋንዳ እና የታንዛኒያ ወታደራዊ ሰልጣኞች የሁለተኛ ዓመት የትከሻ ምልክት ለብሰዋል።

በዕለቱ ተገኝተው የትከሻ ምልክቱን ያለበሱት የኮሌጁ ተወካይ አዛዥ ኮሎኔል አለማየሁ ስበቡ፣ የትከሻ ምልክት ማግኘት ተራ ክስተት ሳይሆን የትጋት፣ የፅናትና የኃላፊነት መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህ የለበሳችሁት ምልክት በኮሌጁ ውስጥ ያሳያችሁትን ስነ-ስርዓትና ውጤታማነት የሚያሳይ ቢሆንም፣ ከፊት ለፊታችሁ ለሚጠብቃችሁ ትልቅ አገራዊና ቀጣናዊ ኃላፊነት የመዘጋጃ የመጀመሪያው እርምጃ ነው በማለት ተናግረዋል።

የኮሌጁ ምክትል አዛዥና የስልጠና ዲን ኃላፊ ኮሎኔል ወልደተክላይ ወልዳይ በበኩላቸው፣ የሁለተኛ ዓመት የትከሻ ምልክት የለበሱ ተማሪዎች የሀገርን አደራና የተቋማቸውን ፍላጎት ግብ ለማድረስ በትጋት መስራት እንደሚኖርባቸው አመላክተዋል።

ዘጋቢ አፈወርቅ በቀለ
ፎቶግራፍ ጥሩወርቅ አናጋው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤20👍12🥰5🔥2👏1
September 18, 2026 3.3K 1