11ኛ ዕዝ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ። የኢፌዴሪ መከላከያ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

11ኛ ዕዝ ለኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት መምሪያ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2019 ዓ.ም

የ11ኛ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ በኮምቦልቻ ከተማ ለሚገኙ 336 ተማሪዎች 224 ደርዘን ደብተርና እስክርቢቶ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲከታተሉ ከማገዝ ባሻገር በእውቀት የበለጸገና ለሀገር ግንባታ የሚያበረክት ትውልድ ለመገንባት የሚደረገው አስተዋፅኦ አካል መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ ላይ የ11ኛ ዕዝ ሎጅስቲክስ ኃላፊ ኮሎኔል እሸቱ ከበደ እንደገለጹት፣ ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ባሻገር ከህዝቡ ጎን በመቆም በትምህርትና በልማት ዘርፎች የበኩሉን አስተዋፅኦ እያደረገ ይገኛል።

የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ሰዒድ ዓሊ በበኩላቸው፣ ሠራዊቱ በልማትና በበጎ ፈቃድ ተግባራት የሚያደርገው ተሳትፎ ህዝባዊነቱንና ወገንተኝነቱን ከማሳየት ባሻገር በሠራዊቱና በህዝቡ መካከል ያለውን ፍቅርና አጋርነት የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል።

የኮምቦልቻ ከተማ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ኢብራሂም አብዱ ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው፣ ድጋፉ ተማሪዎች በእውቀት እንዲበለጽጉና የነገ ሀገር ተረካቢዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያግዝ ተግባር ነው ብለዋል።

በመጨረሻም ሠራዊቱ የሀገርን ሉዓላዊነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በትምህርትና በልማት ዘርፎች የሚያደርገውን ህዝባዊ ተሳትፎ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል። ዘገባው የ11ኛ ዕዝ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍12❤8👏4🔥1😁1
September 5, 2026 3K