በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ እየሠጡ ነው። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ የፅንፈኛው ታጣቂዎች እጅ እየሠጡ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም

በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ዙሪያ ወረዳ በሰራና መረባ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች ለሠራዊታችን እጅ መስጠታቸውን ቀጥለዋል።

በ10ኛ ዕዝ መረጃ ፣በሀገር ሽማግሌዎች እና በወረዳው "ፀጥታ ለሰላም በሰላም" በሚል ሃሳብ በአካባቢው ታጥቀው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የፅንፈኛው ቡድን ታጣቂዎች በሰላማዊ መንገድ እጅ እንዲሰጡ በተደረገው ጥረት 46 ታጣቂዎች ለሰራዊታችን እጃቸው ሰጥተዋል።

በዛሬው እለት እጃቸው የሰጡ ታጣቂዎች ብሬን፣ ስናይፐር፣ ክላሽ እና ኋላ ቀር መሳሪያ ይዘው መግባታቸውን የዕዙ መረጃ ክፍል አስታውቋል።

ታጣቂዎቹ የአካባቢውን ሰላም በማወክ የተሳሳተ ተግባር ላይ እንደነበሩ እና ይህም ለራሳቸው፣ ለቤተሰቦቻቸውና ለአካባቢው እንቅፋት ሆኖው መቆየታቸው አውስተው አሁን ግን ወቅቱን የሚጠብቀው ህዝብን እና መንግስትን በሚጠቅም ስራ በመሰማራት የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡ ገልፀዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ሥነ ልቦና ግንባታ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
👍29❤19👏5🔥2😁1
September 5, 2026 2.9K 2