አሽከርካሪዎች የትራፊክ ህግን በሚገባ ማወቅና መገንዘብ እንደሚገባቸው ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
የ6ኛ ዕዝ ትራንስፖርት ክፍል ለከፍተኛ አመራሮችና ለአሸከርካሪዋች እንዲሁም ለሚመለከታቸው ባለ ድርሻ አካላት የትራፊክ ደህንነትና የጥንቃቄ ደንቦችን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ሰጥቷል።
የዕዙ ሎጅስቲክስ ሃላፊ ኮሎኔል አለማየሁ ነጋሽ የትራፊክ አደጋ መንስኤዋችን ለመከላከል መደረግ ያለባቸው ጥንቃቄዎችን እና መፍትሄዎችን ማወቅና የአሽከርካሪዎችን የስነ ምግባርና የቴክኒክ ብቃት ማረጋገጥ አደጋን ለመቀነስ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል።
አመራሩም ሆነ ሙያተኛው በትራፊክ ደህንነት የጥንቃቄ ጉድለት በሰውና በንብረት ሊደርስ የሚችለውን አደጋ በመከላከልና አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ዕዙ ለሚሰጠው ማንኛውም ግዳጅ ዝግጁ እንዲሆኑና የተሟላ ዕውቀት በመቅሰም ሙያዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የተቋሙን ተሽከርካሪዋችም ሆነ በምንም ነገር ልንተካው የማንችለውን የሠው ህይወት ከትራፊክ አደጋ እንዲሁም ጥንቃቄ ከሚሹ ነገሮች ለመከላከል ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ ኮሎኔል አለማየሁ ነጋሽ አሥገንዝበዋል።
ዘጋቢ ውበቴ አማረ
ፎቶግራፍ ይህአለም አታላይ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
24
14
2
1September 3, 2026 4.6K