የ11ኛ ዕዝ ትራንስፖርት ክፍል ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን አሽከርካሪዎች አስመረቀ። የኢፌዴሪ መከላከያ… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

የ11ኛ ዕዝ ትራንስፖርት ክፍል ለሦስት ወራት ያሰለጠናቸውን አሽከርካሪዎች አስመረቀ።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም

የ11ኛ ዕዝ ትራንስፖርት ክፍል ለወራት በቲዮሪና በተግባር ያሰለጠናቸውን የተሽከርካሪ አሽከርካሪዎች አስመርቋል።

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉትና ለተመራቂ አሽከርካሪዎችና ለሌሎች ድጋፍ ላደረጉ ክፍሎች የምስጋና ሰርተ-ፊኬት የሰጡት የ11ኛ ዕዝ ሎጅስቲክስ ኃላፊ ኮሎኔል እሸቱ ከበደ፣ ብቃት ያላቸው አሽከርካሪዎችን ማፍራት የዕዙን የሎጅስቲክስ አቅም ማጠናከር ለተልዕኮ አፈጻጸም ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።

የዕዙ ትራንስፖርት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል በዛብህ ገረኖ፣ የሥልጠናው ዋና ዓላማ የዕዙን የግዳጅ ሁኔታ መነሻ ያደረገ የአውቶ ሜካኒክ ቲዮሪ፣ የመንገድ ሥነ-ሥርዓት፣ የአንደኛ፣ የሁለተኛና የሦስተኛ ደረጃ አውራ ጎዳና አነዳድ፣ የመሰናክልና የባላንስ ልምምዶችን በቀንና በሌሊት መሰጠቱን ተናግረዋል።

የአዋሽ አርባ ወታደራዊ ተሽከርካሪ አሽከርካሪና ማሽነሪ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ምዘና አስተባባሪ ሻለቃ ባሻ ደምስ ቁምቢ በበኩላቸው፣በ11ኛ ዕዝ ለወራት የሰለጠኑትን አሽከርካሪዎች በቲዮሪና በተግባር መመዘናቸውን አንስተዋል።

እንደ ሻለቃ ባሻ ደምስ ገለጻ፣ በምዘናው ወቅት የቴክኒክ፣ የመንገድ ሥነ-ሥርዓትና ሕግ፣የአውራ ጎዳና አነዳድ እንዲሁም የተለያዩ መሰናክሎችን በተግባር የመቆጣጠር ብቃታቸው ተፈትሿል።

የአዋሽ አርባ ወታደራዊ ተሽከርካሪ አሽከርካሪና ማሽነሪ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የፈተናና ቴክኒክ ሻለቃ ባሻ ሃብታሙ አለሙ በበኩላቸው፣ ተመራቂዎቹ በቴክኒክና በተግባር የተሰጣቸውን ምዘና በማለፍ ተገቢውን የአሽከርካሪነት ብቃት ማሳየታቸውን ገልጸው፣ በቀጣይም ሙያዊ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ መክረዋል። ዘገባው የዕዙ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው፡፡

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤15👍2🔥1
September 1, 2026 2.7K 1