የሎጀስቲክ ዝግጁነት የውጊያ ቁልፍ አቅም መሆኑ ተገለፀ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
የሰሜን ምሰራቅ ዕዝ ሎጀስቲክ ክፍል በግዳጅ ቀጣና በመዘዋወር የኮሩን ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ብቃት አረጋግጧል።
ቡድኑ በዕዙ ስር ከሚገኝ የአንድ ኮር ክፍለጦሮች የግዳጅ ቀጣና በመገኘት ከሠራዊቱ የነብስ-ወከፍ የውጊያ ቁሳቁሶች ጀምሮ በውጊያ ውስጥ ወሳኝ የሆኑ ሎጀስቲካዊ አቅርቦት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ዝግጁነቶችን በፍተሻ አረጋግጧል።
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ሎጀስቲክ ኃላፊ ኮሎኔል ነጋሽ እሬ የኮሩ የሠራዊት ክፍሎች በማንኛውም ሁኔታ የሚገጥማቸውን ጠላት ተዋግተው ማሽነፍ የሚያስችል አስተማማኝ የሎጀስቲካዊ አቅርቦት እና የውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ሙሉ ዝግጁነት እንዳላቸው በፍተሻ መረጋገጡን ገልፀዋል።
የታጠቀውን የውጊያ ማቴሪያል በአግባቡ በመያዝ የተሰጠውን ህዝባዊ አደራ በታላቅ ኃላፊነት መፈፀም የሚችል ጠንካራ ሠራዊት መገንባቱን የጠቀሱት ኃላፊው የውጊያ ቁልፍ አቅም የሆነው ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት መረጋገጡ ለግዳጅ ስኬት ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል ።
ሠራዊታችን በቡድንም ይሁን በነፍስ ወከፍ ደረጃ የሚታጠቃቸው በርካታ ውድ እና ዘመናዊ ትጥቆች ያሉት መሆኑን አውስተው እነዚህን ትጥቆች በእንክብካቤ በመያዝ ዘውትር የውጊያ ዝግጁነታችንን ማረጋገጥ ይኖርብናል ሲሉ አሳስበዋል።
የኮሩ ምክትል አዛዥ ለውጊያ ድጋፍ አገልግሎት ኮሎኔል ፈንታሁን አሊ በበኩላቸው ኮሩ አሁን ያለበትን ወታደራዊ ፣ ስነ- ልቦናዊ እና ሎጀስቲካዊ ዝግጁነት ደረጃ አጠናክሮ በመቀጠል በማንኛውም ግዳጅ ድል አስመዝጋቢ ለመሆን ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል።
ዘጋቢ ሱራፌል መልሰው
ፎቶግራፍ ትዕግስት እናውጋው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
20
13
1September 1, 2026 3.1K