የኢትዮጵያ አየር ኃይል ከ20 ዓመት በታች ወንዶች የእግር ኳስ ቡድን ዋንጫ አነሳ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 26 ቀን 2018 ዓ.ም
በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው የከ20 ዓመት በታች ወንዶች የእግር ኳስ ውድድር፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ንብ አቃቂ ቃሊቲን 1 ለ 0 በማሸነፍ የዋንጫ ባለቤት ሆኗል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ፣ ለንብ አየር ኃይል የማሸነፊያዋን ብቸኛ ግብ ሚኪያስ አበራ በማስቆጠር ቡድኑን የዋንጫ አሸናፊ አድርጓል።
የውድድሩ የበላይነት በንብ አየር ኃይል ቡድን በግልጽ በመንጸባረቁ፣ የኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ ግብ አግቢ እና ኮከብ ግብ ጠባቂ ሽልማቶችንም የንብ አየር ኃይል አባላት በመሆን ተረክበዋል።
በአዲስ አበባ የሚገኙ የአየር ኃይል አባላትና የስፖርት ደጋፊዎችም በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመገኘት ለቡድኑ ያሳዩት የሞራልና የደጋፊነት ስሜት ንብ አየር ኃይል ዋንጫውን እንዲያነሳ አድርጓል።
የአየር ኃይል ንብ ስፖርት ክለብ መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ታዲስ ገብረሚካኤል ከጨዋታው በኋላ በሰጡት አስተያየት፣ ድሉ የአየር ኃይልን የአሸናፊነት ስም ከፍ ያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
ቡድኑ ለዋንጫው እንዲበቃ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የአየር ኃይል አመራሮችና የኮቺንግ ስታፍ አባላትም ምስጋና አቅርበዋል።
ዘጋቢ እሱያውቃል ሙሉዬ
ፎቶ ግራፍ ማማሩ ጌትነት
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
10
9
1September 1, 2026 2.5K 1