ከራስ በላይ ለሀገር የቆሙ የፅናት ማሳያዎች የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የሠው… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ከራስ በላይ ለሀገር የቆሙ የፅናት ማሳያዎች

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የሠው ልጅ በህይወት ዘመኑ በርካታ መሠናክሎችን ያልፋል። በዚህ በመኖር ውስጥ ባለ መሠናክል ለሀገር ብሎ ራስን አሳልፎ ለመሥጠት ያለመ ፈታኝ የህይወት መንገድን ማለፍ ደግሞ ለሀገር ታላቅ ታሪክ ፅፎ ለትውልድ እንደማውረስ ይቆጠራል።

በቃላቶች ሊገለፅ የማይችል አስተዋይን ልቦና በሚከብድ የስሜት ማዕበል የሚያዋኝ ሀገር ማለት እንዲህ ናት ላካ የሚል አንዳች የሃሳብ ባህር ውስጥ የሚዘፍቅ ማሰብን የሚጠይቅ ታላቅ ሥፍራ "አላጌ የጀግኖች አምባ"።

ጀግኖችን ለማወቅ አላጌን ማዬት የግድ አይልም በጀግንነታቸው ልክ ስለእነርሱ ሀገር ወዳድነት፣ ፅናት፣ የአካልና የህይወት መስዋዕትነት፣ ብቻ ሀገር ወዳድነት የሚነገሩ ታሪኮችን በምናብ እየተጓዙ ማድመጥና መንበብ በቂ ሊሆን ይችላል።

አላጌ  የጀግኖች አንባ፤ የጀግንነትን ውድ ዋጋ በጉልህ ይመሰከርበታል። የአላጌ ጀግኖች አምባ የሀገር ህያው ታሪክ የተከተበት፣ የደም ዋጋ የከፈሉ ጀግኖች የተጠለሉበት እና የፅናት ጥበብ የሚታይበት የክብር ማዕከል ነው።

በዚህ አምባ ውስጥ የሚገኙት ጀግኖች ትላንት ለሀገራቸው ሰላም፣ ለነገው ትውልድ ደህንነት ሲሉ ደረታቸውን ለጥይት፣ አካላቸውን ለስለት የሰጡ ታላላቅ ባለውለታዎቻችን ናቸው።

እናት ሀገር በክፉ ቀኗ ስትጠራቸው "እኔ አለሁልሽ!" ብለው ወጣትነታቸውን፣ ምቾታቸውንና ሙሉ አካላቸውን የሰዉ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው።

ዛሬ እነርሱ ጋር የምናየው ጠባሳ የእሳት ቃጠሎ ወይም የአደጋ ምልክት አይደለም፤ የኢትዮጵያ ስም ከፍ ብሎ እንዲኖር የተከፈለ የክብር አሻራ እንጂ!

የሚሰጥ የአካል መስዋዕት የእናት ሀገርን መዋቅር ደግፎ ያቆመ የፅናት ምሰሶ ነው።

እነዚያ በጦር ግንባር የነደዱ ዓይኖች ዛሬም የማዕከሉን ግቢ ሲቃኙ ተስፋን እና የማይበገረውን የኢትዮጵያዊነት ወኔ ያንጸባርቃሉ።

እያገገሙ ያሉት ጀግኖቻችን ዛሬም አልተሸነፉም። የአካል መጉደል የሞራል ስብራት እንዳልሆነ በተግባር እያሳዩን ነው።

በአምባው ውስጥ የሚሰማው የእያንዳንዱ ጀግና ትንፋሽ "ለሀገሬ መኖር ብቻ ሳይሆን መሞትም ኩራት ነው!" የሚል ድምፅ አለው። እነርሱ የወደቁት እኛ ቀና እንድንል ነው። እነርሱ የቆሰሉት ሀገር እንድትድን ነው።

የአላጌ ጀግኖች አምባ የኢትዮጵያ የቁስል ማከሚያ ብቻ አይደለም የአሸናፊነት ወኔ መቅጃ ምንጭ ጭምር ነው። እነዚህ ጀግኖች ስናያቸው ልባችን በትህትና እና በደስታ ቅር ብንሰኝም፣ ወኔያችን ግን እንደ ተራራ ይገዝፋል።

ክብር ለሀገር ጀግኖች! የእናንተ የፅናት፣ የአይበገሬነት፣ የመስዋዕትነት ታሪክ ሁሌም በማይፋቀው መዝገብ ላይ ተከትቦ ለዘላለም ይኖራል። ኢትዮጵያ በጀግንነታችሁ ትኮራለች፣ በትከሻችሁም ላይ ትቆማለች ክብር ለእናንተ ይሁን።

በማሙሽት አድነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤39👏15👎3🔥3
August 30, 2026 5.1K 1