ፈታኝ መልክዓ ምድራዊ ገፅታዎችን በፅናት ተሻግሮ ተልዕኮን በብቃት የመፈፀም ብቃት።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም
በጠንካራ ስነ ልቦናዊ ዝግጁነት ማንኛውንም ፈታኝ መልክዓ ምድራዊ ገፅታዎችን በፅናት ተሻግሮ የሚሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት እንደሚፈፅሙ በግዳጅ ቀጠና የሚገኙ የደቡብ ዕዝ ኮር የሰራዊት አመራርና አባላት ተናግረዋል።
ሠራዊታችን የጠላቶቻችንን እኩይ ሴራ አስቀድሞ በመረዳት ምንጊዜም በሥነ አዕምሮም ሆነ በወታደራዊ አካል ብቃት ዝግጁ መሆናቸዉን የገለፁት የደቡብ ዕዝ ኮር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ኮሎኔል ገብረገርግስ አረጋይ የሀገር ሠላምና ልማት ለማረጋገጥ የሚሰጠንን ማንኛውንም ሀገራዊ ግዳጅ በላቀ ዉጤት ለመፈጸም ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።
የክፍሉ ሠራዊት አባላት ለሀገር ሉዓላዊነትና ለህዝብ ሰላም ዋስትና ናቸዉ ካሉ በኋላ በማንኛውም ወቅትና ሁኔታ ከውጪና ከዉስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ፈተናዎችን በንቃት ለመመከት የሚያስችል የዉጊያ ልምድና ተሞክሮ ያካበቱ እንዲሁም የሞራል የበላይነት የሚጎናፀፉ ተዋጊና አዋጊ መሪዎችን ያቀፈ ክፍል ስለመሆኑ ምክትል አዛዡ አብራርተዋል።
ኮሩ ባለፉት ጊዜያቶች በሰሜን ወሎ ዞን የፅንፈኛ ሃይሎችን በመደምሰስ ያስመዘገበው አመርቂ ዉጤት
እንደ ክፍል በተቀናጀና በተናበበ አኳኋን ጠላት ላይ ባሳየነው የማይበገር ጽናት መሆኑን ጠቅሰዉ በቀጣይ የሚሠጠውን ተልዕኮ ሁሉ ለመፈፀም ዝግጁ ሥለመሆኑ አሥረድተዋል።
ለሀገራችን ታሪክ ክብር እና ለወገኖቻችን ሰላማዊ ኑሮ አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንከፍላለን ያሉት የክፍሉ የሰራዊት አባላት በህዝባችን ላይ በደል ለመፈፀም ለሚንቀሳቀሱ ማናቸዉም ፀረ የሠላም ሃይሎች እድል እንደማይሰጡ አስገንዝበዋል።
የቀደምት አባቶቻችን በፅናት ጠብቀዉ ያቆዩአትን የታላቅ ህዝቦች ሀገር ማንነቷን እና ሉዓላዊነቷን አረጋግጦ ለማሥቀጠል እና ለትዉልድ ለማሻገር የሚጠበቅብንን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ ፈይሳ መልካሙ
ፎቶግራፍ ሰለሞን በዛብህ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
25
11August 30, 2026 4.4K