ተቋማዊ የአይሲቲ ማዕቀፍን በማረጋገጥ ዲጂታል መከላከያን እውን ማድረግ እንደሚገባ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም
"ለወሳኝ ዝግጁነት የመከላከያ አይሲቲ ማዕቀፍን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል የመከላከያ አይሲቲ ማዕከል ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የፖሊሲ እና ስትራቴጂ ማረጋገጫ አውደ ጥናት አካሂዷል።
አውደ ጥናቱ የ2030 የዲጂታል ኢትዮጵያን ስትራቴጂካዊ ዕቅድ መሰረት በማድረግ "ለወሳኝ ዝግጁነት የመከላከያ አይሲቲ ማዕቀፍን ማረጋገጥ" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጅ ሲሆን በአይሲቲው ዘርፍ ለውጥን ማስተዳደር እና መምራት ለማስቻል እንደሆነም በኢትዮ ቴሌኮም የኢንፎርሜሽን ሴኪዩሪቲ ሪኳይርመንት ማናጀር ወይዘሪት ሰላማዊት አሰፋ ገልፀዋል።
የአውደ ጥናቱ ከባለፈው የቀጠለና የአይሲቲ ደህንነት ፖሊሲ ፤ የአይሲቲ አጠቃቀም ፖሊሲ ፤ መሠረታዊ የፖሊሲ ሰነዶች እንዲሁም የስትራቴጂክ የስራ አፈፃፀም ሰነዶች እና የአይሲቲ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በመከላከያ አይሲቲ ማዕከል የዳታ ማዕከል አገልግሎት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ጌቱ ፀጋዬ እንደ ተቋም ከዲጂታል ኢትዮጵያ ዕቅድ ጋር ትስስር ያለውን የአይሲቲ ምህዳር በመዘርጋት የደህንነት እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም፤ የዲጂታል ሉዓላዊነትን በማስጠብቅ፤ የመከላከያን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እውን እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባ ተናግረዋል።
የአይሲቲ አስተዳደር እና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ ዶክተር ሄኖክ ሙሉጌታ በበኩላቸው በዓውደ ጥናቱ ማጠቃለያ ላይ በሰጡት አስተያየት መከላከያ እንደ ተቋም ግዙፍ እና ሀገራዊ ሃላፊነትን የሚወጣ ተቋም በመሆኑ አሁን ላይ ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂዎች በስፋት እየተጠቀመ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተቋሙን አደረጃጀት እና መዋቅር በማጥናት ለተልዕኮ ምቹ የሆኑ የአይሲቲ አስተዳደር ፖሊሲዎችን እና ማዕቀፎችን አዘጋጅተው ለሚመለከታቸው አካላት ለውይይት መቅረቡን ገልጸዋል።
ሰነዶች ጸድቀው ወደ ትግበራ ሲገባ መከላከያን እንደ ተቋም የአይሲቲ መሠረተ ልማቶች ደህንነታቸውን በማስጠበቅ ከውስጥ እና ከውጭ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች መከላከል በሚያስችል ቁመና ላይ መገኘት እንደሚያስችል ተጠቁሟል።
ዘጋቢ ኤሊያስ ከለለኝ
ፎቶግራፍ አብዱልውሀብ ሙእዲን
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
37
13
3
2September 3, 2026 4.5K 5