ክፍለጦሮች ባካሄዱት ኦፕሬሽን በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ ኪሳራ አድርሰዋል። የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

ክፍለጦሮች ባካሄዱት ኦፕሬሽን በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ ኪሳራ አድርሰዋል።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

የሰሜን ምስራቅ ዕዝ እና የ6ኛ ዕዝ ክፍለጦሮች ለሠላም ተገዥ ባልሆነው ፅንፈኛ ቡድን ላይ እርምጃ በመውሰድ ጠላትን ከጥቅም ውጪ ማድረጋቸውን የየክፍለጦር አመራሮች ተናግረዋል።

በራያ ቆቦ ወረዳ ሮቢት አካባቢ በመንቀሳቀስ የህዝቡን ሰላም ሲያውክ በነበረ ፅንፈኛ ቡድን ላይ በተወሠደው እርምጃ በርካቶች ሲደመሰሱ የፅንፈኛ ቡድኑ የሎጅስቲክስ እና የፋይናንስ አስተባባሪ የነበረ ግለሰብ መማረኩን የሰሜን ምስራቅ ዕዝ ክፍለጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽን ሌተናል ኮሎኔል ብሩክ አብርሀም ገልፀዋል።

ሲነር ዋረንት ኦፊሰር ሸጋው ማሞ በበኩላቸው ፅንፈኛው ቡድን ላይ በተወሰደው እርምጃ  ለጥፋት ተልዕኮው ማስፈፀሚያ ሲጠቀምበት የነበረ የነፍስ ወከፍ የጦር መሳሪያ እና ልዩ ልዩ ተተኳሽ እንዲሁም አባሪ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል። ዘገባው የንጉሴ ውብሊቀር ነው።

በተመሳሳይ የ6ኛ ዕዝ ክፍለ ጦሮች ተቀናጅተው  ባደረጉት አሰሳና ስምሪት በምስራቅ ጎጃም ዞን የተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀስ የነበረውን ፅንፈኛ ቡድን ከበባ ውስጥ በማስገባት መደምሰስ መቻሉን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አለምሰገድ ተስፋዬ ገልፀዋል።

በነበረው ኦፕሬሽንም የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ተተኳሽ፣ ትጥቅና የጦር ሜዳ መነፀሮች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች ከ40 ኩንታል በላይ ጤፍና በቆሎ በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን እና በርካታ ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን አዛዡ አስረድተዋል።

ሌተናል ኮሎኔል አለሞ ታምር በበኩላቸው ሠራዊቱ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ የጥፋት ሀይሎች በየትኛውም ቦታ ተሸሽገው ሰላም እንዳያደፈርሱ በንቃት ተልዕኮን በመወጣት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል። የዘገበው ደባልቅ አቤ ነው

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤45👏12👍9😁2
August 30, 2026 4.4K 4