የመኪናዎ ስክሪን ለሳይበር ጥቃት ተጋልጧል? የመኪና ስክሪኖች ላይ የሚሰራጭ አደገኛ ማልዌር ተገኘ፦
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም
የጥቃቱ ምንነት
የካስፐርስኪ የሳይበር ደህንነት ተመራማሪዎች በDoFun የመኪና መዝናኛ ስርዓቶች ላይ የተቃጣ አዲስ ትሮጃን ማልዌር አግኝተዋል። ጥቃቱ የተፈጸመው የመኪናውን የውስጥ ማዘመኛዎች እና ህጋዊውን TWCore መተግበሪያ በመጥለፍ JarService የተሰኘ አደገኛ ሶፍትዌር በመጫን ነው። ዋና ዓላማውም የመኪናውን ስክሪን ተቆጣጥሮ የማስታወቂያ ማጭበርበር (ad fraud) መስራት እና መሳሪያውን የፕሮክሲ ቦትኔት አካል ማድረግ ነው።
የማጥቂያ ዘዴው እና ጉዳቱ
የሳይበር አጥቂዎች በአሁኑ ጊዜ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የሰዎችን ባዮሜትሪክ እና ምስል በመምሰል ሰፊ የመስመር ላይ ማጭበርበሮችን በማካሄድ ላይ ይገኛሉ። ይህ ስጋት አሁን ኢንተርኔት እና SIM ካርድ ወደሚያስፈልጋቸው የመኪና መዝናኛ ስርዓቶች በመሸጋገር፣ ህጋዊ አፕሊኬሽኖችን በመጥለፍ JarService ማልዌርን ይጭናል። በዚህም የባለቤቱን ስክሪን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የማስታወቂያ ማጭበርበር (ad fraud) የሚፈፅሙ ሲሆን፣ መሳሪያውን ለሌሎች ጥቃቶች ፕሮክሲ ቦትኔት ያደርጉታል።
የተበከለው መሳሪያ የመሳሪያውን ዝርዝር መረጃ ለተቆጣጣሪው ሰርቨር በመላክ በየ90 ደቂቃው በሚያደርገው ግንኙነት ተጨማሪ ጎጂ ትእዛዞችን በመቀበል ጥቃቱን ያፋጥናል።
መከላከያ ዘዴ
የመኪናዎን የመረጃና መዝናኛ ስርዓት ከሳይበር ጥቃት ለመጠበቅ የሲስተም updates እና የ-APK መተግበሪያዎችን ከኦፊሴላዊ አምራቾችና ከGoogle Play Store ብቻ ያውርዱ፣ እንዲሁም ያልተረጋገጡ ፋይሎችን በUSB ከመጠቀም ይቆጠቡ።
በተጨማሪም ለመተግበሪያዎች የሚሰጡ ፈቃዶችን በመገደብ መኪናዎን በምስጢር ቁጥር ከተጠበቁ አስተማማኝ የWi-Fi መረቦች ጋር ብቻ ማገናኘት ያስፈልጋል። አጠራጣሪ ማስታወቂያዎች፣ የስክሪን መዘገየት ወይም ከፍተኛ የዳታ ብክነት ሲያጋጥም ወዲያውኑ የፋብሪካ ማስተካከያ (factory reset) ያድርጉ።
የመከላከያ ሳይበር ማዕከል
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
12
9August 30, 2026 3.6K