🗣 ቴዲ ርእዮት ጥያቄ :- "ይህን ስርአት ለመጣል እየተንቀሳቀሱ ያሉትን የ ጥምረት ሀይሎች ለምን አልተቀበልክም። አንድ የአፋብን አመራር በቅርቡ ከአንድ አለም አቀፍ የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ለቀረበለት ጥያቄ ምላሽ ሲሰጥ "የምንታገለው የአማራን ህዝብ ህልውና ለማስከበር ፣ ሀገሪቱን ከመፍረስ ለመታደግ እና የሀገሪቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ነው አላማችን " ብለው ባለበት እናንተ ጥምረቱን ለምን ልትቃወሙ ሞከራቹ?
🗣 ጀዋር መሀመድ ፦ " እነዛ ሀይሎች እነማን ናቸው። ሮድ ማፓቸው ምንድነው" የሚለው እኔን ጭምር ሊያሳምነኝ አልቻለም። ጥምረቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ባልታወቀበት ፣ ጥምረት ፈጥረው ከሆነ በግልጽ እነ እከሌ ተብሎ በመግለጽ በእነሱ መካከል ያለውስ ልዩነት ምን ይመስላል? ለምሳሌ የድምበር ችግሮቻቸውን በምን ይፈታሉ ፣ የአይዲዮሎጂ ልዩነታቸውን በምን ለመፍታት እንዳቀዱ ግልጽ ሊያደርጉ ይገባል። ቀድሞ ሊፈቱ የሚገቡ ጥያቄዎችን አንጠልጥሎ ወደ ጥምረት ከመግባት ይልቅ ቅድሚያ ግልጽ የሆነ የችግር መፍቻ ሰነዳቸውን ለህዝብ በማቅረብ ተነጋግሮ ሊስማሙበት ይገባል ። አንዳንዶች አሁን ላይ ሊፈቱ የሚችሉ ሌሎች ደግሞ ለይደር ተስማምተን የምናቆያቸው ሲሆኑ እነሱን የምንፈታበት ስምምነት ቅድሚያ ሁላችንም በጋራ ተወያይተን የምናቆያቸው ሊሆኑ ይገባል።
በስም የተጠቀሱት የጥምረት አካሎች ጭምር ወጥተው የጥምረቱ አካል መሆናቸውን ባልገለጸበት ሁኔታ በምን አመንክዮ አሉበት ስለ ተባለ ብቻ የተባለውን እናምናለን?"

2
2September 4, 2026 763 1