🚨ጥጋብ እና ርሐብ በኢትዮጵያ!! 🥐🍞
•••••••••••••••••••••••••••
ስማኝ..! ኢትዮጵያ “የተራበች ሀገር” ትባላለች።
ግን ሆቴል ቤቶች፣ ሰርግ ቤቶች፣ እና ድግሶች ላይ የሚጣለውን ምግብ ብታይ… “የጠገበች ሀገር” ትመስላለች። አንድ በኩል እናት “ልጄ ራበኝ” ብላ ታለቅሳለች። ሌላ በኩል ደግሞ አስተናጋጅ ግማሽ የተበላ እንጀራ እና ስጋ ወደ ቆሻሻ ገንዳ ይደፋል። ይሄ አያምም? እኔ ያመኛል! ይሄ እብደት አይደለም?
🟢1. “ይተርፍ እንጂ አይጉደል” መርህ
ድግስ ሲደገስ መፈክራችን “ይትረፍረፍ!” የሚል ነው። ለ500 ሰው ተጠርቶ፣ ለ1000 ሰው ይዘጋጃል። ሰውየው ሳህኑ ላይ ክምር ምግብ ያደርጋል። ግን ሩቡን በልቶ፣ የቀረውን ይተወዋል። ለምን? “የከፈልኩበት ነው” በሚል ትዕቢት!
ወዳጄ… ለምግቡ ብትከፍልም፣ ለምግቡ መፈጠር አልከፈልክም። እህል ከሰማይ ወርዶ፣ ከምድር በቅሎ፣ የገበሬ ላብ ፈሶበት ነው የቀረበልህ። አንተ ግን በአንድ ደቂቃ ውስጥ “ቆሻሻ” አደረግከው። የጣልክው ስጋ፣ የአንድን ህፃን ህይወት ማዳን ይችል ነበር።
የደፋኸው ወጥ፣ የአንድን አረጋዊ ጉልበት ማደስ ይችል ነበር። ብክነት ሀጢአት ነው። ብክነት በድሆች ላይ የሚሰራ ወንጀል ነው።
🔵2. የሆቴል እና የሰርግ ትርኢት
ሰርግ ላይ ኬክ ይቆረሳል። እርስ በርስ ይጎራረሳሉ። የተረፈው ኬክ ምን ይሆናል? ይጣላል? ወይስ ለተራቡ ይሰጣል?
ብዙ ጊዜ ይጣላል። ሆቴሎች “Quality Standard” በሚል ሰበብ፣ የተረፈውን ንፁህ ምግብ ይጥሉታል። በጀርባ በር በኩል ግን ውሾች እና ድመቶች ይበሉታል።
ሰው ከውሻ በታች የሆነበት ዘመን!
ለምን አሰራሩ አይቀየርም? ለምን “የተረፈ ምግብ ባንክ” (Food Bank) አይኖርም?
ለምን ለጎዳና ተዳዳሪዎች በንፅህና ተዘጋጅቶ አይሰጥም? ችግሩ የምግብ እጥረት ሳይሆን፣ የልብ እጥረት ነው።
🟣3. የቁጠባ ባህል ማጣት
ቤት ውስጥም ብንሆን… ዳቦ ይሻግታል፣ ወጥ ይበላሻል። ፍሪጅ ውስጥ ምግብ አስቀምጠን እንረሳዋለን። ቆይቶ ሲወጣ ይሸታል፣ ይጣላል።
ይሄ ሁሉ ብር እኮ ነው። የገንዘብ ኖት (Note) ቀደህ እንደመጣል ማለት ነው። የኢኮኖሚ ቀውስ አለ እያልን፣ በሌላ በኩል ሀብታችንን በቆሻሻ መኪና እንልካለን። ስማኝ አንተ ስግብግብ ሳህንህ ላይ የምትጨርሰውን ያህል ብቻ ቀንሰህ ብላ። የተረፈህን ለእንስሳት ወይም ለተቸገረ ሰው ስጥ። ግን አትጣል።
♦️ ወንድሜ…⚠️
ምግብ ስትጥል፣ የተራበውን ልጅ ፊት አስታውስ።
ኬክ ስትደፋ፣ የደረቀውን የቦረና መሬት አስታውስ።
ፈጣሪ የሰጠህን በረከት የምትጥል ከሆነ፣ ነገ አንተም ትጣላለህ።
“የጠገበ ምን ይላል?” አትሁን።
ከማይጠቅም ድግስ፣ የሚጠቅም ምጽዋት ይበልጣል!
🫵🏻 Via, [ጦማሪው ፈላስፋው ጭሰኛ] ✍🏻
.
.
ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
📌 t.me/Fastsinfo99
🌴 🌴 🌴
Telegram
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa.
✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን
✅|| write to us if you have any comments or complaints.
👀 @Fastmereja_Bot 👀

3August 26, 2026 718 2