ስለ ማፈያ አባሉና ገ ዳ ዩ #ባይሳ ቀልቤሳ የማዕረግ እድገት ጉዳይ .. ባይሳ ቀልቤሳ የኦሮሚያ ፖሊስ 20ኛ… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

ስለ ማፈያ አባሉና ገ ዳ ዩ #ባይሳ ቀልቤሳ የማዕረግ እድገት ጉዳይ ..

ባይሳ ቀልቤሳ የኦሮሚያ ፖሊስ 20ኛ ዙር አባል ነው። 20ኛው ዙር በ2008 ዓ.ም በሰንቀሌ እና ለጋ ዳዲ ማሰልጠኛ ሰልጥኗል። ይህም ማለት የኦሮሚያ ፖሊስ አባል ከሆነ ገና 10 ዓመቱ ነው።
በኦሮሚያ ፖሊስ መመሪያ መሠረት አንድ የፖሊስ አባል የማዕረግ እድገት በሁለት መንገዶች ያገኛል። እነሱም መደበኛ እና አስቸኳይ ሂደቶች ናቸው።

አንድ አባል ከኮንስታብል ተነስቶ ረዳት ኢንስፔክተር ለመድረስ በመደበኛ ሂደት 11 ዓመታት ሲያስፈልገው፣ በአስቸኳይ ሂደት ደግሞ 7 ዓመታትን ይወስዳል። እዚህ ላይ አንድ ሰው በፖሊስ ኮሌጅ ተወዳድሮ ከተማረ ከዚህ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከፍተኛ ማዕረግ ማግኘት ይችላል። አንድ አባል ከዋና ሳጅንነት ወደ ረዳት ኢንስፔክተርነት ለመሸጋገር ብቃቱ እና ሥነ-ምግባሩ ተመዝዝኖ፣ የሚሰጠውን ፈተና አልፎ ለወራት የሚቆይ ሥልጠና በፖሊስ ኮሌጅ መውሰድ ግዴታ ነው።

ረዳት ኢንስፔክተር የሆነ አባል ደግሞ ምክትል ኮማንደር ለመድረስ በመደበኛ ሂደት 11 ዓመታት፣ በአስቸኳይ ሂደት ደግሞ 7 ዓመታት ያስፈልገዋል። አንድ አባል ከኢንስፔክተርነት ወደ ዋና ኢንስፔክተርነት ለማደግ ብቃቱ እና ሥነ-ምግባሩ ተመዝዝኖ የሚሰጠውን ፈተና ካለፈ፣ ወደ ፖሊስ ኮሌጅ በመግባት የሚሰጠውን ሥልጠና ወስዶ ማዕረጉን ያገኛል።

በኦሮሚያ ፖሊስ መመሪያ ቁጥር 104 መሠረት፣ ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ወይም ስኬት ያስመዘገበ አባል የአንድ ደረጃ የማዕረግ እድገት በሽልማት መልክ ሊያገኝ ይችላል።

#ኮማንደር_ባይሳ_ቀልቤሳ
በኦሮሚያ ፖሊስ መመሪያ መሠረት ባይሳ ከኮንስታብል ተነስቶ ረዳት ኢንስፔክተር ለመድረስ በመደበኛ ሂደት 11 ዓመታት፣ በአስቸኳይ ሂደት ደግሞ 7 ዓመታት ይወስድበታል። ከረዳት ኢንስፔክተርነት ወደ ምክትል ኮማንደርነት ለመድረስ በመደበኛ ሂደት 11 ዓመታት፣ በአስቸኳይ ሂደት 7 ዓመታት ይወስዳል። በአጠቃላይ ከኮንስታብል ማዕረግ እስከ ምክትል ኮማንደር ለመድረስ በመደበኛ ሂደት 22 ዓመታት፣ በአስቸኳይ ሂደት ደግሞ 14 ዓመታት ይወስዳል። ባይሳ የፖሊስ አባል ከሆነ ግን 10 ዓመት ብቻ ነው።

ከባይሳ ጋር አብረው የሰለጠኑት (20ኛው ዙር) አባላት ገና አሁን ረዳት ኢንስፔክተር ማዕረግ ላይ እየደረሱ ይገኛሉ። ታዲያ ባይሳ በምን መስፈርት ነው በ10 ዓመታት ውስጥ ምክትል ኮማንደር ሊሆን የቻለው? በዚህ ጉዳይ ላይ ከኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የውስጥ መረጃ የተገኙ ጥቂት ክፍተቶችን እና መመሪያውን በመጣስ የተሰሩ ሥራዎችን ለመመልከት፦

* ባይሳ ከዋና ሳጅንነት ወደ ረዳት ኢንስፔክተርነት ለማደግ ማሟላት የሚገባውን መስፈርት አላሟላም። ወደ ኦሮሚያ ፖሊስ ማሰልጠኛ ገብቶ ምንም ዓይነት የመኮንንነት ትምህርት አልተማረም። እንዴት ወደዚህ ማዕረግ ሊሸጋገር ቻለ?

* ባይሳ ተወዳድሮ የፖሊስ ሙያ ብቃቱን የሚያጎለብት ትምህርት ፖሊስ ኮሌጅ ገብቶ ለመማሩ የሚያሳይ ነገር የለም። በዚህም መንገድ የተጨመረለት ማዕረግ የለም። ቢኖር እንኳ በ10 ዓመታት ውስጥ ምን ዓይነት ትምህርት? ስንት ጊዜ? ተምሮ ነው ይህንን ማዕረግ ያከማቸው የሚለው ጥያቄ ነው።

* ባይሳ ከኢንስፔክተርነት ወደ ዋና ኢንስፔክተርነት ለመሸጋገር የሥራ ብቃቱ እና ሥነ-ምግባሩ ታይቶ፣ አስፈላጊውን ፈተና ተፈትኖ በማለፉ ለሥልጠና በ1/5/2018 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ኮሌጅ ገባ። እዚህ ላይ የሥራ ብቃቱ እና ሥነ-ምግባሩ ምን ይመስላል ብለን ብንጠይቅ በሚዲያ ሲነገር የነበረው ይታወቃል።

ሆኖም ያንን ሥልጠና ወስዶ ዋና ኢንስፔክተር ከሆነ ከ4 ወራት በኋላ ምክትል ኮማንደርነት ማዕረግ ተሰጠው። እሱም ስሙ በተለያዩ ወንጀሎች በሚዲያ እየተነሳ ባለበት ወቅት።

* ባይሳ በሽልማት እንኳ ተሰጥቶት ቢሆን፣ በየትኛው መመሪያ መሠረት ነው በ10 ዓመታት ውስጥ ምክትል ኮማንደር ሊደርስ የቻለው የሚለው ጥያቄ ነው!

በአጠቃላይ የባይሳ ቀልቤሳ የማዕረግ እድገት ሁኔታ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽኑ ሕገ-ወጥ እና በማፊያ ቡድኖች የተያዘ መሆኑን የሚያሳይ ነው።

Via [©Gurmuu Oromiyaa] 🤘
.
.

ለተጨማሪ መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ

📌 t.me/Fastsinfo99

    🌴  🌴  🌴
Telegram
𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
✅|| 𝐘𝐀𝐀𝐃𝐀 ykn komii yoo qabaattan nuuf barreessaa. ✅|| ማንኛውም አስተያየት ወይም ቅሬታ ካለዎት ይፃፉልን ✅|| write to us if you have any comments or complaints. 👀 @Fastmereja_Bot 👀
❤4
August 26, 2026 733