የአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲ አይ ኤ) ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ሞስኮ ውስጥ ከሩስያ የደህንነት ባለስልጣናት… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🚨🇺🇸🇷🇺 የአሜሪካው የስለላ ድርጅት (ሲ አይ ኤ) ዳይሬክተር ጆን ራትክሊፍ ሞስኮ ውስጥ ከሩስያ የደህንነት ባለስልጣናት ጋር መነጋገራቸውን ክሬምሊን አስታወቀ። የሁለቱ ኃያላን የደህንነት ባለስልጣናት ውይይት የተካሄደው በዩክሬን ያለው ጦርነት እየተባባሰ በመጣበት እና በአሜሪካና በኢራን መካከል ዘላቂ ሰላም ለማውረድ የሚደረገው ጥረት ዉጤት ባጣበት ወቅት ነው።
የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚርፑቲን ስለውይይቱ የተደረገላቸውን ገለጻ ከመስማት ባሻገር ከአሜሪካው የደህንነት ሃላፊ ጋር እንዳልተገናኙ ነው የተሰማው።
የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲሚትሪ ፔስኮቭ ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት የደህንነት ተቋማት መካከል የተደረገ መሆኑን ከመግለጽ ውጭ ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።
ፔስኮቭ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የተበላሸ ግንኙነት ማስተካከል ስለመቻሉ ከወዲሁ መናገር «አስቀድሞ መደምደም ይሆናል» ብለዋል።
እንደዚያም ሆኖ የደህንነት ተቋማቱ ግንኙነት ግን በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት« በጣም አስቸጋሪ በሚባሉ ጊዜያት እንኳ ሳይቋረጥ የሚቀጥል» እና በራሱ አዎንታዊ እርምጃ እንደሆነ ሳይናገሩ አላለፉም።
በተጨማሪም ፔስኮቭ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት የገባበትን ጥልቅ ውጥረት ለመቅረፍ ውይይቱ ምን ያህል ሚና ይኖረዋል የሚለውም ወደ ፊት እንደሚታይ ነው የገለጹት ።
የሩሲያ ባለስልጣናት በሁለቱ ሀገራት የደህንነት መስሪያ ቤቶች መካከል የሚደረጉ ቀጥተኛ ግንኙነቶች አሁንም አስፈላጊ መሆናቸውን አጽንኦት ሰጥተውበታል።
ጆን ራትክሊፍ የሲ አይ ኤ ዳይሬክተር ከሆኑ ወዲህ ወደ ሩሲያ ሲጓዙ የመጀመሪያቸው ነው። ሲ አይ ኤ ከሞስኮ የደህንነት ኃላፊዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዳለው ይነገራል።

~ምንጭ፡ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል፣ ብሎምበርግ፣ ዋሽንግተን ፖስት እና ዶቼቬሌ ናቸው🤘
.
.
ቴሌግራም፦
            📌t.me/Brics4ethiopia
Telegram
BRICS 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
𝐁𝐑𝐈𝐂𝐒 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 ____ 👉 | እኛ ገለልተኛ የሚዲያ ኩባንያ ነን 👉 | አለምአቀፍ ሰበር ዜናዎች እና 👉 | ጂኦፖለቲካ ፣ ደህንነትና የሚ/ትንተና 👉 | በ BRICS ቻናላችን ላይ ያገኛሉ ____ 👉 | Nuti miidiyaa walabaati. 👉 | ji’oopoolitikaa ፡nageenya fi 👉 | Xinxala miidiyaalee 👉 | "BRICS" n irraa...
❤1
August 26, 2026 778 1