📈 News_Jobs/$$FX: post #2012 — TG.ME

መንግሥት 7 የክሪፕቶ ካረንሲ መተግበሪያዎች በሀገር ውስጥ እንዳይሠሩ ሙሉ በሙሉ መታገዳቸውን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

መተግበሪያዎቹ ለሕገወጥ የገንዘብ ዝውውር ሽፋን ይሰጡ እንደነበር አመልክቷል።

ከዚህ ቀደም የተለያዩ የክሪፕቶ ከረንሲ መተገበሪያዎች የኢትዮጵያን ብር ከP2P መድረክ ላይ ማስወጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (EEP) ተገቢው መመሪያ በሌለበት ሁኔታ ከ36 የዳታ ማይኒንግ ድርጅቶች ጋር ሕገ-ወጥ የኃይል ሽያጭ ውል የፈጸሙ 4 ከፍተኛ አመራሮች ላይ እርምጃ መወሰዱን አመልክቷል።

በሌላ በኩል፤ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር፣ በሐዋላ እና በጥቁር ገበያ ተሳታፊ የሆኑ 169 ኢትዮጵያውያንና የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ ተጠያቂ እንዲሆኑ መደረጉን አሳውቋል።

በተጨማሪ በተደራጀ መንገድ ከንግድ ባንክ ደንበኞች አካውንት ላይ በማጭበርበር ገንዘብ የወሰዱ 36 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው የባንክ ሒሳባቸው እንዲታገድ ተደርጓልም ብሏል።

Join us. 
Join ➣ https://t.me/exitfx
Join ➣ https://t.me/exitfx


https://t.me/exitfx
August 7, 2026 291