ቅዱሳን ሐዋርያትም ‹‹ከ #አብ የሠረፀ የሁላችንም መጽናኛ የሚሆን ዓለሙንም ሁሉ ያዳነ ከ #አብና ከ #ወልድ ጋር ህልው የሚሆን #መንፈስ_ቅዱስን ላከልን፡፡ #መንፈስ_ቅዱስ #ጰራቅሊጦስም አንድ ነው›› ብለዋል። በሌላም ነቢዩ ዳዊት ስለ #መንፈስ_ቅዱስ ‹‹መንፈስህን ከእኔ አታርቅ አለ፤ ዳግመኛም በሰውነቴ እውነተኛ መንፈስን አጽናልኝ፣ ከሁሉ በሆነ #መንፈስ_ቅዱስ አጽናኝ አለ›› በማለት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ #መንፈስ_ቅዱስን ጰራቅሊጦስ አጽናኝ መካሪ መባሉን አስተምሯል። (መዝ. ፶፥ ፲-፲፪፤ መጽሐፈ ምሥጢር)
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በበዓለ ኀምሳ ምንባብ ላይ #እግዚአብሔር_መንፈስ_ቅዱስ #ጰራቅሊጦስ ስለተባለበትና ተስፋ በተሰጣቸው በኀምሳኛው ቀን ወርዶ ስለ ሠራው ሥራ እንዲህ በማለት ያብራራል። ‹‹ወ #መንፈስ_ቅዱስኒ ኢተሰምየ #ጰራቅሊጦስሃ ዘእንበለ አመ ይቤሎሙ #እግዚእ_ኢየሱስ ለአርዳኢሁ እፌኑ ለክሙ ካልአ #ጰራቅሊጦስሃ። #ጰራቅሊጦስ ብሂል ናዛዚ ብሂል በነገረ ጽርዕ …… #መንፈስ_ቅዱስም #ጌታ_ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ሌላውን አጽናኝ እልክላችኋለሁ›› ከማለቱ በፊት #ጰራቅሊጦስ አልተባለም #ጰራቅሊጦስ ማለት በጽርዕ ቋንቋ አጽናኝ ማለት ነው ስለምን አጽናኝ ተባለ ደቀ መዛሙርቱ #ወልድ ካረገበት ቀን ጀምሮ #ጰራቅሊጦስ እስከ ወረደበት ቀን ድረስ ያለቅሱ ነበረና ስለዚህም #ወልድ #መንፈስ_ቅዱስን_ጰራቅሊጦስ አለው። የስሙ ትርጓሜ ግን አስቀድመን እንደተናገርነው አጽናኝ ማለት ነው። (ዮሐ. ፲፬፥፲፭)
#በዓለ_ጰራቅሊጦስ የሚከበረው ርደተ #መንፈስ_ቅዱስን መሠረት በማድረግ በመሆኑ ምክንያት ጸጋ #መንፈስ_ቅዱስ ለመቀበል ነው፤ በዕለቱም ኢየሩሳሌም በተባለችው #ቤተ_ክርስቲያን ስለመጽናት፤ ከግለኝነት ይልቅ መንፈሳዊ አንድነትን ስለማስቀደም እና ስለመጸለይ እንማራለን፡፡
በዓለ ትንሣኤውን በቸርነቱ በሰላም እንድናሳልፍ ፈቅዶ እስከ ዛሬ ድረስ ስለ ጠበቀን፣ አሁን ደግሞ በጾም፣ በጸሎት ሆነን እርሱን የምናመሰግንበትን ወቅት ስላመጣልን #አምላካችን_ልዑል_እግዚአብሔር ስሙ ለዘለዓለሙ የተመሰገነ ይሁን፤ አሜን፡፡
➣ምንጮች፤ መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፲፰ ቀን፣ መጽሐፈ ምሥጢር፡፡መጽሐፈ ግጻዌ...፡፡
ወስብሐት ለ #እግዚአብሔር
#መልካም_በዓል








