ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ ++++++++++++… — Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ — TG.ME

ከፍተኛ ዉጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎቻችን እንኳን ደስ አላችሁ - ከንቲባ አዳነች አቤቤ
++++++++++++

#ጋዜጣ_ፕላስ - በ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 32 ነጥብ 3 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ 1ኛ ደረጃን መያዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንደገለፁት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው፤ የዛሬ 12 ዓመት ያቋቋምነው የኦሮሚያ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ዘንድሮም ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100% ማሳለፍ ችሏል።

ተማሪ ጃለላ ግርማ ኩሳ 591.6 ወጤት በማምጣት እንደ ሀገር ከፍተኛ ነጥብ በማስመዝገብ አንደኛ ወጥቷል።

በከተማ አስተዳደሩም የእቴጌ መነን የሴቶችና ገላን የወንድ ተማሪዎች አዳሪ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 24 ትምህርት ቤቶች ያስፈተናቸውን ተማሪዎች 100 ፐርሰንት ማሳለፍ ችለዋል ብለዋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ ሳይንስ ከሴት ተማሪዎች መካከል ከፍተኛው ውጤት 569.1 ያመጣችዉ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኘው ከቦሌ ሱፕር ሆሊ ሴቪየር ት/ቤት ተማሪ መቅደላዊት ሱራፌል ማሞ መሆኗንም ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቀጣይ ከዚህ የላቀ ውጤት ለማስመዝገብ የተጀመረውን ስትራቴጂ በአግባቡ መተግበር፣ የትምህርት አመራሮች፣ ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራት፣ ወላጆች ለተማሪዎች ውጤት መሻሻልና ለትምህርት ልማት ስራው ስኬት ባለቤት ሆኖ መስራትና ተማሪዎች ለላቀ ውጤት መትጋት ይጠበቅባቸዋል።
❤7
August 25, 2026 2.5K