የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮው ማየት ይቻላል - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች… — Gazette Plus / ጋዜጣ ፕላስ/ — TG.ME

የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤትን ዛሬ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮው ማየት ይቻላል
- የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
+++++++++++

ጋዜጣ_ፕላስ- የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤት የሚገለጽበት አድራሻ ይፋ ማድረጉን የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አስታወቀ

በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎችን በመጠቀም ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ 19 እስከ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል እንደሚችሉ አመልክቷል።

#Ethiopia #ExaminationResult #12Class #ExamResult #education #EthiopiaProgress
❤1
August 25, 2026 2K 6