ለአዲስ ዓመት በዓል ገበያ በቂ ዝግጅት ተደርጓል አለ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ… — Ethio Fm 107.8 — TG.ME

Ethio Fm 107.8Photo
ለአዲስ ዓመት በዓል ገበያ በቂ ዝግጅት ተደርጓል አለ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በመጪው አዲስ ዓመት በዓል ገበያ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት የሚታይባቸውን መሰረታዊ የምግብ ምርቶች በቂ አቅርቦት ማዘጋጀቱን አስታወቀ።

የቢሮው ኃላፊ ወ/ሮ ሀቢባ ሲራጅ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ከ3 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ708 ሺህ ኩንታል በላይ ቀይ ሽንኩርት እና 227 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ ለበዓሉ ገበያ እንደሚቀርብ ተናግረዋል።

በተጨማሪም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ዶሮዎች፣ ከ42 ሚሊዮን በላይ እንቁላሎች፣ እንዲሁም 2 ሚሊዮን የሚጠጉ በግና ፍየሎች ለገበያ እንደሚቀርቡ ታውቋል።

ምርቶቹን ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማዳረስም 5 የቀንድ እንስሳት መሸጫ ማዕከላት እና 264 የቅዳሜና እሁድ ገበያዎች በሳምንቱ ሙሉ ክፍት ሆኖ እንዲሰሩ መወሰኑን የቢሮው ኃላፊ ገልጸዋል።

በተጨማሪም ለህብረተሰቡ በጥራትና በበቂ ሁኔታ ለማዳረስ ሲባል የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም የፋብሪካ ምርቶች መሸጫ ማዕከላት አገልግሎቱ እንዲሰጡ ይደረጋል ተብሏል።


ሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
September 1, 2026 1.8K 5