የኩላሊት ታካሚዎች በመድኃኒት ዋጋ መናር እና በትራንስፖርት እጥረት እየተፈተኑ መሆኑን ገለጹ የተስፍ የኩላሊት… — Ethio Fm 107.8 — TG.ME

የኩላሊት ታካሚዎች በመድኃኒት ዋጋ መናር እና በትራንስፖርት እጥረት እየተፈተኑ መሆኑን ገለጹ

የተስፍ የኩላሊት የታካሚወች  ማህበር የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ባህይሉ እረና እንደገለፁት የኩላሊት ታካሚዎች ከሕመማቸው በተጨማሪ በመድኃኒት ዋጋ መጨመር እና በትራንስፖርት ችግር ከፍተኛ እንግልት እየደረሰባቸው መሆኑን ተናግረዋል

በተለይም ለሕክምናቸው ወሳኝ የሆነው የ"ሄፓሪን" መድኃኒት ዋጋ በአሁኑ ወቅት እስከ 800 ብር ድረስ መድረሱ ታካሚዎችን ለከፍተኛ ችግር ዳርጓቸዋል ብለዋል።

ማህበሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለታካሚዎች በማህበሩ መታወቂያ ነፃ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያመቻች ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች የሚመጡ ታካሚዎች ቁጥር ከፍተኛ መሆኑን የገለጸው ማህበሩ፣ በነዚህ አካባቢዎች የበሽታው መስፋፋት መንስኤ ላይ ጥናት እንዲደረግና መንግስት ለመድኃኒት አቅርቦትና ለቦታ አቅርቦት ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቋል።

ሊዲያ ደሳለኝ

ነሐሴ 30/2018 ዓ.ም
September 5, 2026 1.7K 3