የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ጊዜ ተራዘመ አለ ከተማ አስተዳደሩ የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት… — Ethio Fm 107.8 — TG.ME

የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ጊዜ ተራዘመ አለ ከተማ አስተዳደሩ

የአከራይና ተከራይ ውል ምዝገባና እድሳት የመጨረሻ ጊዜ እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. መራዘሙን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው የጊዜ ገደቡን ያራዘመው በተለያዩ ምክንያቶች ውላቸውን ማደስ ያልቻሉ አከራዮችና ተከራዮች በመኖራቸውና ከህብረተሰቡ በቀረቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች መሆኑን ገልጿል።

በመሆኑም ውላቸውን ያላደሱ ሁሉም አከራዮች እና ተከራዮች እስከ ጳጉሜ 5 ድረስ በክፍለ ከተሞች፣ በመሶብ አንድ ማዕከላትና ለአገልግሎቱ በተዘጋጁ ቦታዎች በመቅረብ ውላቸውን እንዲያድሱ ቢሮው ጥሪ አቅርቧል።

ነሐሴ 30 /2018 ዓ/ም
September 5, 2026 733 5