በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመት 32 ሺህ 134 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ኢነርጂ ለማመንጨት መታቀዱን… — Ethio Fm 107.8 — TG.ME

በአዲሱ የ2019 በጀት ዓመት 32 ሺህ 134 ጊጋ ዋት ሰዓት ኤሌክትሪክ ኢነርጂ ለማመንጨት መታቀዱን  በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኃይል ማመንጫዎች  ኦፕሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር እያየሁ ሁንዴሳ እንደገለፁት፤ ከታቀደው ጠቅላላ ኃይል ውስጥ፦ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ 44 በመቶ፣ጊቤ ሦስት 19 ነጥብ 3 በመቶ፣በለስ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ደግሞ 7 ነጥብ 8 በመቶ ድርሻ ይኖራቸዋል።

በክረምቱ ወራት ያጋጠመውን የዝናብ እጥረት ለማካካስም ልዩ ጥብቅ የውሃ አጠቃቀምና የተቀናጀ የግድብ ውሃ አስተዳደር ተግባራዊ እንደሚደረግ ተመላክቷል።

እስከ ጥቅምት ወር ያለውን የዝናብ ስርጭት በመገምገም የማመንጨት ዕቅዱ ሊከለስ እንደሚችል የጠቆሙት ሥራ አስፈፃሚው፤ ዕቅዱን ለማሳካት አንድም ኪሎ ዋት ሳያባክኑ ጣቢያዎችን ዝግጁ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ከተቋሞ የማህበራዊ ገጽ እንዳገኘነው መረጃ ለዚህም የቅድመ መከላከል፣ የፍተሻና የጥገና ሥራዎች በልዩ ትኩረት እየተከናወኑ ይገኛሉ።

ነሐሴ 23/2018 ዓ.ም
August 29, 2026 1.6K 1