በመዲናዋ ብቃታቸው የተረጋገጠ ከ4 መቶ በላይ ስፔሻላይዝድ የጥርስ ህክምና ተቋማት መኖራቸው ተገለፀ ‎… — Ethio Fm 107.8 — TG.ME

Ethio Fm 107.8Photo
በመዲናዋ ብቃታቸው የተረጋገጠ ከ4 መቶ በላይ ስፔሻላይዝድ የጥርስ ህክምና ተቋማት መኖራቸው ተገለፀ

‎የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን በከተማዋ 4መቶ2 ብቃታቸው የተረጋገጠ ስፔሻላይዝድ የጥርስ ህክምና ተቋማት መኖራቸውን አስታውቋል።

‎ባለስልጣኑ የሚቆጣጠራቸውን እነዚህን ተቋማት እውቅና ለመስጠት መዘጋጀቱንም ገልጿል።

‎ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከሮቫ ኤቨንትስ እና መልቲሚዲያ ጋር በመተባበር በጥርስ ሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የላቀ ሥራ ላከናወኑ የጥርስ ሕክምና ተቋማትና ባለሙያዎች ያዘጋጀውን የእውቅና እና የሽልማት መድረክ ይፋ አድርጓል።

‎ፕሮግራሙ በታካሚ እንክብካቤ፣ በክሊኒካዊ ብቃት፣ በንጽህና እና በማህበረሰብ ላይ አዎንታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ረገድ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ተቋማትን እውቅና መስጠትን ግብ ያደረገ ነው።

‎ፕሮግራሙ እውቅና ከመስጠት ባለፈ ሰፊ ሀገራዊ ፋይዳ እንዳለው
‎ ተነስቷል።

‎የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉእመቤት ታደሰ፥ የዕውቅናው አላማ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ የጥርስ ሕክምና ማዕከላት እንዲስፋፉ ማድረግ እንደሆነ አንስተዋል።

‎15 የዕውቅና መስፈርቶች መኖራቸው የተገለፀ ሲሆን፥ ተቋማቱ ከአንድ በላይ በሆኑ መስፈርቶች መወዳደር እንደሚችሉ ተነስቷል።

‎ለዚህ ሲባል የተዘጋጀ ዌብሳይት መኖሩም ተገልጿል።

‎የዕውቅና ሽልማቱ 70 በመቶ በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ግምገማ እና 30 በመቶ በህዝብ ድምፅ እና ምርጫ የሚደረግ ይሆናል።

‎በየዓመቱ ደረጃውን እና ፕሮፌሽናሊዝምን በጠበቀ መልኩ የሚከናወን መርሀ ግብር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

‎ሽልማቱ በጥቅምት 2019 የሚካሄድ መሆኑም ተገልጿል።

‎እስከዳር ግርማ

‎ነሐሴ 26/2018 ዓ.ም
September 1, 2026 1.1K 7