በሳምንቷ የተገኘችው የ7 ዓመቷ ሕፃን ናኒ!
ነሐሴ 22 ቀን አመሻሽ ላይ በእናቷ ስልክ ወደ እኛ የተደወለው ስልክ በጭንቀት የተሞላ ነበር።
“ልጃችን ከቦሌ ቡልቡላ አካባቢ እየተጫወተች ሳለ ጠፋችብን፤ እባካችሁን አፋልጉን!”
የ7 ዓመቷ ናኒን ከምትጫወትበት ቦታ ይዛ የጠፋችው ሰው የቤታቸው ሠራተኛ መሆኗ ተረጋገጠ። እንደተገለጸው፣ ሕፃኗን በሌሊት ወደ ደብረ ማርቆስ ይዛ በመሄድ፣ ባሕር ዳርን አቋርጣ ጎንደር ከገባች በኋላ ከተባባሪዎቿ ጋር በመሆን 3 ሚሊዮን ብር ቤዛ ጠይቃለች ተብሏል።
የተጨነቁት እናትና አባት የልጃቸውን ድምፅ ከሰሙ በኋላ 400,000 ብር መላካቸው ተገልጿል። በፍርሃትና በጭንቀት የተሞሉት ወላጆች ልጃቸውን በሕይወት ለማግኘት ተስፋ አልቆረጡም።
በቀጣዮቹ 7 ቀናት በተካሄደ የተቀናጀ ክትትልና ኦፕሬሽን፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን፣ ኢንሳ እና ሪፐብሊካን ጋርድ በጋራ ባደረጉት ሥራ ሕፃኗ ናኒ በመጨረሻ ተገኝታለች።
የቤት ሠራተኛዋም ሕፃኗን ይዛ በነበረችበት ሁኔታ መያዟ ተገልጿል። ከጠለፋው ጋር ተያይዘው 14 ተጠርጣሪዎች መያዛቸውም ታውቋል።
ለተሳተፋችሁት ሁሉ ክብርና ምስጋና ቀርቧል!
ሕፃኗን በሕይወት ለማስመለስ የተባበሩትን ተቋማትና የጸጥታ አካላት ማመስገን ይገባል።
የናኒ አባት አቶ ሰለሞንም ለተደረገላቸው ትብብርና ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፦
-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja
57
5
1
1September 4, 2026 5.9K 6 4




