በተቀጠረች በ4ኛው ቀን የስርቆት ወንጀል የፈፀመችው የቤት ሰራተኛ በፅኑ እስራት ተቀጣች።
***
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27 ቀን 2018 ዓ/ም (አዲስ ፖሊስ)፦ ተከሳሽ መልካም አያልነህ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ቻይና ካምፕ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
ተከሳሿ በቤት ሰራተኝነት ተቀጥራ ስትሰራ ከነበረችበት መኖሪያ ቤት ውስጥ በተቀጠረች በ4ኛው ቀን አሰሪዎቿ በተኙበት አጋጣሚ ቻርጅ ላይ የነበረ 85 ሺህ ብር የሚገመት አልትራS 21 የሆነ ሞባይል እና የተለያዩ አልባሳትን ሰርቃ ተሰውራለች።
ከግል ተበዳይ ጥቆማው የደረሰው የጅማ በር አካባቢ ፖሊስ መምሪያም የምርመራና ክትትል ቡድን በማቋቋም ግለሰቧን ለመያዝ ባደረገው ብርቱ ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከተሰወረችበት ቦታ በቁጥጥር ስር በማዋል የተሰረቀውን ሞባይል ማስመለስ እንደተቻለ ፖሊስ መምሪያው አስታውቋል።
በግለሰቧ ላይ አስላጊውን ምርመራ ከተጣራ በኃላም የምርመራ መዝገቡን ለአቃቤ ህግ በመላክ ክስ እንዲመሰረትባት መደረጉን ፖሊስ ገልጿል።
የተከሳሽ መልካም አያልነህን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ኮልፌ ቀራንዮ ምድብ ፈጣን ወንጀል ችሎት ጥፋተኝነቷን በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች ካረጋገጠ በኋላ ተከሳሿን ያስተምራል ሌሎች ወንጀል ፈፃሚዎችን ያስጠነቅቃል በማለት በፈፀመችው የስርቆት ወንጀል በ5 አመት ከ7 ወር ፅኑ እስራት እንድትቀጣ ውሳኔ አስተላልፎባታል።
በቤት ሰራተኝነት ከተቀጠሩ በኃላ የተለያዩ ወንጀሎችን ፈፅመው የሚሰወሩ በመኖራቸው አሰሪዎች የቅርብ ክትትል ከማድረግ ጀምሮ ለንብረታቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስቧል።
-ETHIO-MEREJA-
T.me/ethio_mereja
50
8
6
1September 2, 2026 10.7K 4 11

