ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ከ700 በላይ ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ተያዙ፡፡… — ETHIO-MEREJA® — TG.ME

ቀረጥ ሳይከፈልባቸው ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ ከ700 በላይ ተንቀሳቃሽ ስልኮችና ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ተያዙ፡፡

ተገቢውን የጉምሩክ ሂደት ያላለፉና በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ የተለያዩ ዓይነትና መጠን ያላቸው ከ700 መቶ በላይ የሞባይል ቀፎዎች፣ ከሁለት ሺህ በላይ የቻርጀር ገመዶች፣ ልዩ ልዩ የኤሌክትሮኒክስ መለዋወጫዎችና አልበሳት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የመሣለሚያ አካባቢ ፖሊስ መምሪያ ነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ/ም በክ/ከተማው ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል ከምሽቱ 1፡00 ሠዓት ሲሆን አሰፋ ጸጋ እና አማኑኤል ብርሀኑ የተባሉ ተጠርጣሪዎች የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን የሠሌዳ ቁጥር B-77746 አ.አ በሆነ ሱዙኪ የጭነት ተሽከርካሪ ይዘው ሲንቀሳቀሱ ስራ ላይ በነበሩ የፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የክ/ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያ በተጠርጣሪዎቹ ላይ ተገቢውን የሰውና የሰነድ ማስረጃ በማደራጀት ክስ እንደሚያስመሰርት የገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡም መሰል የወንጀል ድርጊት በሀገር ምጣኔ ሀብትና በህጋዊ ነጋዴዎች ላይ የሚያሳድረውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመረዳት የመረጃ የመስጠት ባህሉን ሊያጠናክር እንደሚገባም የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

(ምንጭ ፣ አዲስ አበባ ፖሊስ)

      -ETHIO-MEREJA-
     T.me/ethio_mereja
❤32😢4
August 31, 2026 10.5K 2 11