🏗️በሳይት ላይ የኮንክሪት ድብልቅ (Site Concrete Mixing & Quality Control) ሲከናወን ሊደረጉ የሚገቡ ወሳኝ ጥንቃቄዎች!
🏛በምስሎቹ ላይ እንደሚታየው በሳይት ደረጃ በሞተር በሚሰራ ሚክሰር (Concrete Mixer) ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠር እና ውሃ ተጨምረው ለስትራክቸር ስራ የሚሆን ኮንክሪት በመደባለቅ ላይ ይገኛሉ።
📌 በሳይት ደረጃ ለጥራት እና ለኮንክሪት ጥንካሬ (Concrete Strength) ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦
1️⃣ የተመጣጠነ ስብጥር (Proper Mix Proportions): በዲዛይኑ መሠረት (ለምሳሌ C25 ወይም C30) የተቀመጠውን የሲሚንቶ፣ አሸዋ እና ጠጠር መጠን በጥብቅ መከተል። የቁሳቁሶቹን መጠን በድምፅ (Volume Batching/Gauge Box) ወይም በሚዛን (Weight Batching) በትክክል መስፈር ተገቢ ነው።
2️⃣ የውሃ እና ሲሚንቶ- (Water-Cement Ratio): የውሃ መጠን ከመጠን በላይ መጨመር የኮንክሪቱን ጥንካሬ (Strength) በከፍተኛ ሁኔታ ስለሚቀንስና ስሊት/ክራክ እንዲፈጠር ስለሚያደርግ አስፈላጊውን የመስሪያ ምቹነት (Workability) ብቻ በሚሰጥ መጠን ማስተካከል ያስፈልጋል።
3️⃣ የመደባለቂያ ጊዜ (Mixing Duration): ቁሳቁሶቹ በሚክሰሩ ውስጥ ከተጨመሩ በኋላ ኮንክሪቱ አንድ አይነት ቀለም እና ስብጥር (Uniform Consistency) እስኪያገኝ ድረስ በቂ ጊዜ (ከ 1.5 እስከ 2 ደቂቃ) መደባለቅ አለበት።
4️⃣ የሰራተኞች ደህንነት (PPE & Safety): ሲሚንቶ እና አቧራ ለሳንባ እና ለቆዳ ጎጂ በመሆናቸው ሰራተኞች የአፍ መሸፈኛ (Dust Mask)፣ ጓንት እና ተገቢውን የደህንነት አልባሳት መጠቀም አለባቸው።
@etconp

4
1August 31, 2026 905 4